ኦ ፡ ክብር (O Keber)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ኦ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ ለሆነው ፡ አንበሳ ፡ ለሌለው ፡ አምሳያ
ልበል ፡ ላመስግነው ፡ ከአንጀቴ
ውለታው ፡ ስለበዛ ፡ የመድሃኒቴ

ሳላውቀው ፡ ያወቀኝ ፡ ሳልሻው ፡ ያዳነኝ
በአስገራሚ ፡ ፍቅሩ ፡ እኔን ፡ የወደደኝ
ከጥፋት ፡ እሩጫ ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ኢየሱስ ፡ ነውና ፡ ያወጣኝ ፡ ከእሳት

አዝ፦ ኦ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ ለሆነው ፡ አንበሳ ፡ ለሌለው ፡ አምሳያ
ልበል ፡ ላመስግነው ፡ ከአንጀቴ
ውለታው ፡ ስለበዛ ፡ የመድሃኒቴ

በልጅነት ፡ ጊዜ ፡ ያኔ ፡ በለጋነት
ጠላት ፡ ሲጐትተኝ ፡ ወደ ፡ እዛ ፡ ባርነት
ፀጋው ፡ ባይበዛልኝ ፡ እጁ ፡ ባይደግፈኝ
የት ፡ ቦታ ፡ ነበርኩኝ ፡ ክንፉ ፡ ባይጋርደኝ

አዝ፦ ኦ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ ለሆነው ፡ አንበሳ ፡ ለሌለው ፡ አምሳያ
ልበል ፡ ላመስግነው ፡ ከአንጀቴ
ውለታው ፡ ስለበዛ ፡ የመድሃኒቴ

ጥሩር ፡ ሆኖልኛል ፡ በጦርነት ፡ ጊዜ
ፍለጻ ፡ ሲያቆስለኝ ፡ በሃዘን ፡ ትካዜ
ውለታውን ፡ እያሰብኩ ፡ ላመስግነው ፡ ጌታን
አይገኝምና ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚረዳኝ

አዝ፦ ኦ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ሃሌሉያ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ ለሆነው ፡ አንበሳ ፡ ለሌለው ፡ አምሳያ
ልበል ፡ ላመስግነው ፡ ከአንጀቴ
ውለታው ፡ ስለበዛ ፡ የመድሃኒቴ