ኦ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ልራመድ (O KeEgziabhier Gar Leramed)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ! ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ልራመድ
ሔኖክ ፡ በሄደበት ፡ መንገድ
ደካማ ፡ እጄን ፡ ይዘህ ፡ ምራኝ
በጣፋጭ ፡ ድምፅህ ፡ ምከረኝ
መንገዱ ፡ እንዳይጠፋብኝ
መድኅን ፡ ኢየሱስ ፡ አትለየኝ

አልችልም ፡ ብቻዬን ፡ ልሄድ
ሲንዣበብ ፡ የሰማይ ፡ ሞገድ
ተጠምደው ፡ ሳለ ፡ ሺህ ፡ ወጥመዶች
ከበውኝ ፡ ሳለ ፡ ሺህ ፡ ጠላቶች
ጸጥ ፡ አድርግና ፡ ይህን ፡ ሞገድ
ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ !
አብረን ፡ እንሂድ

እጄን ፡ በጅህ ፡ ላይ ፡ አድርጌ
የምድርንም ፡ ተድላ ፡ ንቄ
በድፍረት ፡ እራመዳለሁ
መስቀልህን ፡ እሸከማለሁ
ወደ ፡ ጽዮን ፡ በር ፡ እስክደርስ
ጌታ ፡ ሆይ !
አብረን ፡ እንጓዝ