From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x)
አደራረግህ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው
እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
1. ሰው ፡ በቃ ፡ ብሎ ፡ የገነዘውን
ድንጋይ ፡ አትሞ ፡ የቀበረውን
መቃብር ፡ ከፍተህ ፡ ድንጋይ ፡ ፈነቀልህ
መግነዘን ፡ ፈተህ ፡ በነጻ ፡ ለቀህ
በሕይወት ፡ ታኖራለህ
አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x)
አደራረግህ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው
እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
2. አሥራ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ ደሜ ፡ እጅግ ፡ ፈሷል
ሐብቴም ፡ ንብረቴም ፡ በከንቱ ፡ አልቋል
ተስፋ ፡ የለህሽም ፡ በቃ ፡ ያሉኝ
ጌታዬን ፡ ዳስሼ ፡ ፈውስ ፡ አገኘሁኝ
ተመስገን ፡ አልኩኝ
አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x)
አደራረግህ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው
እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
3. ተስፋ ፡ ተቆርጦ ፡ ምን ፡ ይሁን ፡ ሲባል
እምነት ፡ ሲጠፋ ፡ ጉልበትም ፡ ሲዝል
በተዘጋ ፡ በር ፡ በድንገት ፡ ገብተህ
በሚያበራ ፡ ልብስ ፡ በክብር ፡ ተገልጠህ
ታሳርፋለህ
አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x)
አደራረግህ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው
እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
4. ብዙዎች ፡ እያሉ ፡ የተከበሩ
በዕውቀት ፡ ያጌጡ ፡ በወርቅ ፡ በብሩ
እንደ ፡ እኔ ፡ ያለ ፡ ደካማን ፡ መርጠህ
ብርቱን ፡ አሳፈርክ ፡ ስምህን ፡ አክብረህ
አንተ ፡ ድንቅ ፡ ነህ
አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x)
አደራረግህ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው
እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
|