ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በምሕረትህ (O Gieta Hoy Bemehereteh)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በምሕረትህ
ወደ ፡ አንተ ፡ አቅርበን
በሥራችን ፡ የጠፋን ፡ ነን
በፀጋህ ፡ አድነን

ሃጥያታችን ፡ ይቅር ፡ በለን
አሁን ፡ ተቀበለን
በዚህ ፡ ዓለም ፡ አትተወን
ወደ ፡ አንተ ፡ ውሰደን

ኦ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መለኮት
ና ፡ ና ፡ ውረድልን
በኃይልህም ፡ አነቃቃን
ለጽድቅህም ፡ አብቃን

የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ሃሌሉያ
በደምህ ፡ የዋጀኸን
ዛሬም ፡ ደግሞ ፡ አትለየን
አሜን ፡ ለዘላለም