ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው (O Gerum Hayl New)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው (፪x)
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ በክንድህ ፡ ውስጥ ፡ ያለው
ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው

ፀሐይ ፡ ከዋክብትን ፡ በአየር ፡ አንሳፈሃል
መሬትን ፡ በድምቀት ፡ በውበት ፡ ፈጥረሃል
ነፋስን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እንዲኖር ፡ አዘሃል
ክበር ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ክቡር ፡ ኃይል ፡ ለብሰሃል

አዝኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው (፪x)
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ በክንድህ ፡ ውስጥ ፡ ያለው
ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው

ለአበቦች ፡ መዓዛን ፡ ለእንስሳት ፡ ማደሪያን
ለወፎች ፡ ጐጆ ፡ ለአራዊት ፡ ጫካን
ለዓሣ ፡ ባሕርን ፡ መኖሪያ ፡ አድርገሃል
ክበር ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ክቡር ፡ ኃይል ፡ ይዘሃል

አዝኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው (፪x)
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ በክንድህ ፡ ውስጥ ፡ ያለው
ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው

ተራራ ፡ ሸንተረር ፡ ወንዙን ፡ ሜዳውንም
ፈጥረሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሚሳንህ ፡ የለም
ጥበብን ፡ ለሰው ፡ ልጅ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ሰጥተሃል
ክበር ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ክቡር ፡ ኃይል ፡ ይዘሃል

አዝኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው (፪x)
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ በክንድህ ፡ ውስጥ ፡ ያለው
ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው