ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ ሳስብ (O Eyesus Hoy Anten Saseb)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ልቤ ፡ ይደሰታል
ፊትህን ፡ ማየት ፡ ግን ፡ ይበልጣል ፡ ዕረፍትም ፡ ይሰጣል
የትሁታንም ፡ ተስፋ ፡ ሆይ ፡ የገሮችም ፡ ደስታ
ለወደቁት ፡ ሁሉ ፡ ቸር ፡ ነህ ፡ መልካምም ፡ ለሚሹህ
የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ፍቅር ፡ ካልቀመሱት ፡ በቀር
ለመግለጽ ፡ የማይቻል ፡ ነው ፡ በቃል ፡ በመናገር
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ደስታችን ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ቤዛችን ፡ ነህ
ክብራችን ፡ በአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም
|