ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ ፡ በዘማሪ ሽዋዬ ዳምጤ (Nuro Kegieta Keyesus Gara)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በሸለቆም ፡ ይሁን ፡ በተራራ
አመቺ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ያሰኛል (፪x)
እርካታን ፡ ይሰጣል

የሰው ፡ ልጅ ፡ ባከማቸው ፡ ንብረት ፡ ሰላምን ፡ አግኝቶ ፡ ቢሆን ፡ ኖሮ
አይሰማም ፡ ነበር ፡ ከዓለም ፡ የሃዘን ፡ እንጉርጉሮ
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ያከማቸ ፡ እርሱ ፡ ይሰበስባል
የያዘው ፡ የረዘዘው ፡ ሁሉ ፡ እርካታን ፡ ይሰጠዋል

አዝ፦ ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በሸለቆም ፡ ይሁን ፡ በተራራ
አመቺ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ያሰኛል (፪x)
እርካታን ፡ ይሰጣል

ወርቅ ፡ አንጥፈው ፡ አልማዝ ፡ ደርበው ፡ ብርን ፡ ተንተርሰው ፡ ቢተኙትም
የእረፍት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሌለ ፡ የሰላም ፡ እንቅልፍ ፡ የለም
ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቤትን ፡ ካልሰራ ፡ የሰው ፡ ድካም ፡ ከንቱ ፡ ነው
ዘለቄታ ፡ ያለው ፡ ሰላምና ፡ በረከት ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በሸለቆም ፡ ይሁን ፡ በተራራ
አመቺ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ያሰኛል (፪x)
እርካታን ፡ ይሰጣል

በዓለም ፡ ፍፁም ፡ ገነው ፡ ቢታዩም ፡ ጽኑ ፡ ክቡር ፡ ሃያል ፡ ቢባሉ
የመንፈስ ፡ እረፍት ፡ አይገኝም ፡ ካልመጣ ፡ ከመስቀሉ
ግባ ፡ መሬት ፡ አይቀርምና ፡ በሞት ፡ ጥላ ፡ ማለፉ
ሰው ፡ በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ካልዳነ ፡ የእሳት ፡ ባሕር ፡ ነው ፡ ትርፉ

አዝ፦ ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በሸለቆም ፡ ይሁን ፡ በተራራ
አመቺ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ያሰኛል (፪x)
እርካታን ፡ ይሰጣል

እኔስ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አለኝ ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁኝ ፡ ምስኪን ፡ ድሃ
ነፍሴን ፡ ዕለት ፡ ዕለት ያረካታል ፡ በጣፋጭ ፡ የሕይወት ፡ ውሃ
በምድርም ፡ ሳለሁኝ ፡ ይመስገን ፡ ለነፍሴ ፡ ዋስትና ፡ አላት
ድንኳኔም ፡ ቢፈርስ ፡ ጌታ ፡ ይክበር ፡ አለኝ ፡ የከበረ ፡ ቤት

አዝ፦ ኑሮ ፡ ከጌታ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋራ
በሸለቆም ፡ ይሁን ፡ በተራራ
አመቺ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ያሰኛል (፪x)
እርካታን ፡ ይሰጣል