ኑ ፡ ሁላችን ፡ እንመልከት (Nu Hulachen Enmelket)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኑ ፡ ሁላችን ፡ እንመልከት
የጌታችንን ፡ ሥቃይ
ኃጢአትን ፡ ሲያስወግድ
መከራውን ፡ እንወያይ
የጌታችንን ፡ ሕመም
የሚመስል ፡ አልነበረም

ቅዱስ ፡ አካሉን ፡ ችንካሩ
ገትሮ ፡ አቆሰለ
የእሾህ ፡ ዘውድ ፡ ነው ፡ በግምባሩ
መቅሠፍትም ፡ ተቀበለ
የጌታችንን ፡ ሕማም
የሚመስል ፡ አልነበረም

በመጨረሻም ፡ በመስቀል
እጅግ ፡ ከተሣቀየ
አሁን ፡ መንፈሴን ፡ ተቀበል
ሲል ፡ ለአባቱ ፡ ጸለየ
የጌታችንን ፡ ሕማም
የሚመስል ፡ አልነበረም

የአምላክ ፡ መቅደስ ፡ መንጦላዕት
ያን ፡ ጊዜ ፡ ተቀደደ
የማስታረቅም ፡ መሥዋዕት
ፈጽሞ ፡ ተጨረሰ
የጌታችንን ፡ ሕማም
የሚመስል ፡ አልነበረም

ሰው ፡ ሆይ! ስለ ፡ ኃጢአትህ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሞቷል
እስከ ፡ መስቀል ፡ ሞት ፡ ጥፋትህ
መድኅኑን ፡ አድርሷል
የኢየሱስን ፡ ፍቅርም
የሚመስል ፡ አልነበረም