ኑ ፡ እናንት ፡ ሰዎች (Nu Enant Sewoch)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኑ ፡ እናንት ፡ ሰዎች
ጌታን ፡ እናመስግን
አብራችሁም ፡ ልጆች
አመስግኑ ፡ ፍቅሩን
አክብሩ ፡ ፀጋውን

ሰማይና ፡ ምድር
በግርማ ፡ ሲሞላ
የሰማይ ፡ ክብር
ትቶ ፡ በትሕትና
ስለ ፡ እኛ ፡ ተገዛ

ያን ፡ ደዌያችንን
እርሱ ፡ ተሸከመ
ኃጢአትን ፡ አሸነፈ
ሰላሙን ፡ ሰጠነ

እኛን ፡ ሊበጀን
ንጹሑ ፡ ቆሰለ
ለእርሱ ፡ ሊዋጀን
እጅግ ፡ ተጋደለ
በመስቀሉ ፡ ሞተ

ሊያዘጋጀን
ሙሽራው ፡ ልንሆን
ሞገስ ፡ ሊሰጠን
በሥሙ ፡ ስናምን
ጽድቁን ፡ ተላብሰን

በቃል ፡ በሥራ
ኢየሱስን ፡ ለማክበር
በሞቀ ፡ ደስታ
ስለ ፡ አምላክ ፡ ፍቅር
በመዝሙር ፡ እናክብር