ኑ ፡ ደካሞች ፡ ሁላችሁ (Nu Dekamoch Hulachihu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኑ ፡ ደካሞች ፡ ሁላችሁ
ወደ ፡ ምሉዕ ፡ ሰላም
ሕይወት ፡ የሚሰጣችሁ
ወረታ ፡ አይሻም
ግሩም ፡ ነው ፣ የምሕረተኛ
የፍቅሩ ፡ ትሩፋት
የሚሰጠነ ፡ ለእኛ
በፀጋው ፡ ብዛት

ኢየሱስን ፡ እየው ፡ ቶሎ
አሁን ፡ ይጠራሃል
ብትዘገይስ ፡ ቶሎ
ዘመንህ ፡ ያልፋል
ፍቅሩን ፡ አትናቀው
አሁን ፡ ተቀበለው
ገዝቶሃልና ፡ ለርሱ
ልብህን ፡ ስጠው

ቸኩል ፡ ወደርሱ ፡ አሁን
አንተን ፡ ይጠብቃል
የተዘጋጀ ፡ ክብሩን
ያቀርብልሃል
ባዶ ፡ ምስኪን ፡ መሆንህን
እርሱ ፡ በጣም ፡ ያውቃል
የሚያስፈልግህን
ወዶ ፡ ይሰጣል