ለመሆኑ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ምን ፡ ይላል (New page Under Construction)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ለመሆኑ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ምን ፡ ይላል?
የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ምንድነው?
በመጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ እንዲህ ፡ ተጽፏል:_

ዮሐንስ ፡ ወንጌል ፡ ፩ ፡ ፩ ፡ _ ፭
በመጀመሪያው ፡ ቃል ፡ ነበረ ፣
ቃልም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ነበረ ፣
ቃልም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበረ ።
ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ሆነ ፣ ከሆነውም ፡ አንዳች ፡ስንኳ
ያለእርሱ ፡ አልሆነም ። በእርሱ ፡ ሕይወት ፡ ነበረች ፣
ሕይወትም ፡ የሰው ፡ ብርሃን ፡ ነበረች ።
ብርሃንም ፡ በጨለማ ፡ ይበራል ፣ ጨለማም ፡ አላሸነፈውም ።

ዮሐንስ ፡ ወንጌል ፡ ፩ ፡ ፲፬
ቃልም ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፣ ፀጋንና ፡ ዕውነትንም ፡ ተመልቶ ፡ በእኛ ፡ አደረ ፣
አንድ ፡ ልጅም ፡ ከአባቱ ፡ ዘንድ ፡ እንዳለው ፡ ክብር ፡ የሆነውን ፡ ክብሩን ፡ አየን ።

ዮሐንስ ፡ ወንጌል ፡ ፫ ፡ ፲፮
በእርሱ ፡ የሚያምን ፡ ሁሉ ፡ የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ እንዲኖረው ፡ እንጂ
እንዳይጠፋ ፣ እግዚአብሔር ፡ አንድያ ፡ ልጁን ፡ እስኪሰጥ ፡ ድረስ ፡
ዓለሙን ፡ እንዲሁ ፡ ወዶአልና ።

ኢሣያስ ፡ ፳፭ ፡ ፱
በዚያም ፡ ቀን: ፡_ እነሆ ፡ አምላካችን ፡ ይህ ፡ ነው ፤ ተስፋ ፡ አድርገነዋል ፣
ያድነንማል ፤ እግዚአብሔር ፡ ይህ ፡ ነው ፤ ጠብቀነዋል ፤ በማዳኑ ፡ ደስ ፡ ይለናል ፣
ሐሤትም ፡ እናደርጋለን ፡ ይባላል ።

ኢሣያስ ፡ ፵፭ ፡ ፲፰
ሰማያትን ፡ የፈጠረ ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱም ፡ ምድርን ፡ የሠራና ፡ ያደረገ ፣ ያጸናትም ፣ መኖሪያም ፡ ልትሆን ፡ እንጂ ፣
ለከንቱ ፡ እንድትሆን ፡ ያልፈጠራት ፡ አምላክ ፡ እንዲህ ፡ ይላል:_ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነኝ ፤ ከእኔም ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ የለም ።

ዮሐንስ ፡ ወንጌል ፡ ፰ ፡ ፲፪
ደግሞም ፡ ኢየሱስ ፡ _ እኔ ፡ የዓለም ፡ ብርሃን ፡ ነኝ ፣
የሚከተለኝ ፡ የሕይወት ፡ ብርሃን ፡ ይሆንለታል ፡ እንጂ
በጨለማ ፡ አይመላለስም ፡ ብሎ ፡ ተናገራቸው ።

ዮሐንስ ፡ ወንጌል ፡ ፰ ፡ ፴፩
ኢየሱሥም ፡ ያመኑትን ፡ አይሁድ:_ እናንተ ፡ በቃሌ ፡ ብትኖሩ
በዕውነት ፡ ደቀ ፡ መዛሙርቴ ፡ ናችሁ ፣ ዕውነትንም ፡ ታውቃላችሁ ፣
ዕውነትም ፡ አርነት ፡ ያወጣችኋል ፡ አላቸው ።

ዮሐንስ ፡ ወንጌል ፡ ፰ ፡ ፴፬ _ ፡ ፴፮
ኢየሱስ ፡ መለሰ ፡ እንዲህ ፡ ሲል:_ ዕውነት ፡ ዕውነት ፡ እላችኋለሁ ፣
ኃጢአት ፡ የሚያደርግ ፡ ሁሉ ፡ የኃጢአት ፡ ባርያ ፡ ነው ።
ባርያም ፡ ለዘላለም ፡ በቤት ፡ ዓይኖርም ፤ ልጁ ፡ ለዘላለም ፡ ይኖራል ።
እንግዲህ ፡ ልጁ ፡ አርነት ፡ ቢያወጣችሁ ፡ በዕውነት ፡ አርነት ፡ ትወጣላችሁ ።

ሐዋርያት ፡ ሥራ ፡ ፪ ፡ ፴፰ _ ፡ ፴፱
ጴጥሮስም:_ ንስሐ ፡ ግቡ ፣ ኃጢአታችሁም ፡ ይሰረይ ፡ ዘንድ
እያንዳንዳችሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሥም ፡ ተጠመቁ ፤
የመንፈስ ፡ ቅዱስንም ፡ ሥጦታ ፡ ትቀበላላችሁ ። የተስፋው
ቃል ፡ ለእናንተና ፡ ለልጆቻችሁ ፣ ጌታ ፡ አምላካችንም ፡ ወደ ፡ እርሱ
ለሚጠራቸው ፡ በሩቅ ፡ ላሉ ፡ ሁሉ ፡ ነውና ፡ አላቸው ።

፩) እግዚአብሔርን ፡ ብቻ ፡ አምልኩ
   ከእኔ ፡ በቀር ፡ ሌሎች ፡ አማልክት ፡ አይሁኑልህ! ዘጸአት ፡ ፳ ፡ ፫

ከላይ ፡ በሰማይ ፡ ካለው ፡ በታችም ፡ በምድር ፡ ካለው ፡ ከምድርም ፡ በታች ፡ በውኃ ፡ ካለው ፡ ነገር ፡ የማናቸውንም ፡ ምሣሌ ፡ የተቀረጸውንም ፡ ምሥል ፡ ለአንተ ፡ አታድርግ ። አትስገድላቸው ፡ አታምልካቸውምም ፤ በሚጠሉኝ ፡ እስከ ፡ ሦስተኛና ፡ እስከ ፡ አራተኛ ፡ ትውልድ ፡ ድረስ ፡ የአባቶችን ፡ ኃጢአት ፡ በልጆች ፡ ላይ ፡ የማመጣ ፣ ለሚወዱኝ ፡ትዕዛዜንም ፡ ለሚጠብቁ ፡ እስከ ፡ ሺህ ፡ ትውልድ ፡ ድረስ ፡ ምሕረትን ፡ የማደርግ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ቀናተኛ ፡ አምላክ ፡ ነኝና ። ፡ ፡ ዘጸአት ፡ ፳ ፡ ፬ _ ፯
እኔ ፡ ግን ፡ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ ጀምሬ ፡ አምላክህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነኝ ፤ ከእኔም ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ አታውቅም ፣
ከእኔም ፡ በቀር ፡ ሊላ ፡ መድኃኒት ፡ የለም ። በምድረ ፡ በዳ ፡ እጅግ ፡ በደረቀ ፡ ምድር ፡ አውቄህ ፡ ነበር ። ከተሰማሩ ፡ በኋላ ፡
ጠገቡ ፣ በጠገቡም ፡ ጊዜ ፡ ልባቸው ፡ ታበየ ፤ ስለዚህ ፡ ረሱኝ ። ፡ ፡ ፡ ፡ ሆሴዕ ፡ ፲፫ ፡ ፬ ፡ _ ፮

፪) እግዚአብሔርን ፡ ውደዱ
  ኢየሱሥም ፡ መልሶ ፡ እንዲህ ፡ አለው:_ ከትዕዛዛቱ ፡ ሁሉ ፡ ፊተኛይቱ:_ እሥራኤል ፡ ሆይ! ስማ ፣ ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንድ ፡ ጌታ ፡ ነው ፤ አንተም ፡ በፍፁም ፡ ልብህ ፡ በፍፁምም ፡ ነፍስህ ፡ በፍፁምም ፡ ሃሣብህ ፡ በፍፁምም ፡ ኃይልህ ፡ ጌታ ፡ አምላክህን ፡ ውደድ ፡ የምትል ፡ ናት ። ፊተኛይቱ ፡ ትዕዛዝ ፡ ይህች ፡ ናት ። ማርቆስ ፡ ፲፪ ፡ ፴

፫) ሁለተኛይቱም ፣ ባልንጀራህን ፡ እንደ ፡ ራስህ ፡ ውደድ ፣ የምትል ፡ እርሷን ፡ የምትመስል ፡ ይህች ፡ ናት ። ከእነዚህ ፡ የምትበልጥ ፡ ሌላ ፡ ትዕዛዝ ፡ የለችም ። ማርቆስ ፡ ፲፪ ፣ ፴፩

አቤቱ ፡ የቤትህን ፡ ሥፍራ ፣ የክብርህንም ፡ ማደሪያ ፡ ወደድሁ ። መዝሙር ፡ (፳፮) ፡ ፰

፫) እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑት
እግዚአብሔርን ፡ በመሰንቆ ፡ አመስግኑት ፣ አሥር ፡ አውታርም ፡ ባለው ፡ በበገና ፡ ዘምሩለት ። አዲስ ፡ ቅኔም ፡ ተቀኙለት ፣ በዕልልታም ፡ መልካም ፡ ዝማሬ ፡ ዘምሩ ። መዝሙር ፡ (፴፫) ፡ ፪ _ ፫

ሁልጊዜ ፡ ስለ ፡ ሁሉ ፡ በጌታችን ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሥም ፡ አምላካችንንና ፡ አባታችንን ፡ ስለ ፡ ሁሉ ፡ አመስግኑ ። ፡ ፡ ኤፌሶን ፡ ፭ ፡ ፳

፬) እግዚአብሔርን ፡ ፍሩ
   የጥበብ ፡ መጀመሪያ ፡ እግዚአብሔርን ፡ መፍራት ፡ ነው ፤ ሰነፎች ፡ ግን ፡ ጥበብንና ፡ ተግሣጽን ፡ ይንቃሉ ። ልጄ ፡ ሆይ ፣ የአባትህን ፡ ምክር ፡ ስማ ፣ የእናትህንም ፡ ሕግ ፡ አትተው ፤ ለራስህ ፡ የሞገስ ፡ ዘውድ ፡ ለአንገትህም ፡ ድሪ ይሆንልሃልና ። ምሣሌ ፡ ፩ ፡ ፯ እስከ ፡ ፰

እንዲህም ፡ ሆነ ፤ አዋላጆች ፡ እግዚአብሔርን ፡ ስለፈሩ ፡ ቤቶችን ፡ አደረገላቸው ። ዘጸዐት ፡ ፩ ፡ ፳፩

በሦስተኛውም ፡ ቀን ፡ ዮሴፍ ፡ እንዲህ ፡ አላቸው ፤ ትድኑ ፡ ዘንድ ፡ ይህን ፡ አድርጉ ፤ እኔ ፡ እግዚአብሔርን ፡ እፈራለሁና ። ዘፍጥረት ፡ ፵፪ ፡ ፲፰ ።

ሙሴም ፡ ለሕዝቡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሊፈትናችሁ ፣ ኃጢአትንም ፡ እንዳትሠሩ ፡ እርሱን ፡ መፍራት ፡ በልባችሁ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፡ መጥቶአልና ፡ አትፍሩ ፡ አለ ። ዘጸአት ፡ ፳ ፡ ፳

እግዚአብሔር _ ሕዝቡን ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሰብስብ ፣ በምድርም ፡ በሕይወት ፡ በሚኖሩበት ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ እኔን ፡ መፍራት ፡ ይማሩ ፡ ዘንድ ፡ ልጆቻቸውንም ፡ ያስተምሩ ፡ ዘንድ ፡ ቃሌን ፡ አሰማቸዋለሁ ። ዘዳግም ፡ ፬ ፡ ፱

በራስህ ፡ አስተያየት ፡ ጠቢብ ፡ አትሁን ፣ እግዚአብሔርን ፡ ፍራ ፣ ከክፋትም ፡ ራቅ ። ይህም ፡ ለሥጋህ ፡ ፈውስ ፡ ይሆንልሃል ። ለአጥንትህም ፡ ጠገን ። ምሣሌ ፡ ፫ ፡ ፯ ፡ _ ፰

በአንተ ፡ ለሚያምኑ ፡ በሰው ፡ ልጆች ፡ ፊት ፡ ያዘጋጀሃት ፣ ለሚፈሩህም ፡ የሰወርሃት ፡ ቸርነትህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ በዛች ። መዝሙር፡ (፴፩) ፡ ፲፱

 ስምህን ፡ ለመፍራት ፡ ልቤ ፡ ደስ ፡ ይለዋል ። መዝ (፹፮) ፡ ፲፩

 ሰማይ ፡ ከምድር ፡ ከፍ ፡ እንደሚል ፡ እንዲሁ ፡እግዚአብሔር ፡ ምሕረቱን ፡ በሚፈሩት ፡ ላይ ፡ አጠነከረ ። ፡ ፡ መዝሙር ፡ (፻፫) ፡ ፲፩

ሁለተኛው ፡ ግን ፡ መልሶ:_ አንተ ፡ እንደዚህ ፡ ባለ ፡ ፍርድ ፡ ሳለህ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ከቶ ፡ አትፈራውምን? ብሎ ፡ ገሠጸው ። ሉቃስ ፡ ፳፫ ፡ ፵
፭)
፮) ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቅረቡ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል ፣ መታመኛዬም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፣ በጽዮን ፡ ልጅ ፡ በሮች ፡ ምሥጋናህን ፡ ሁሉ ፡ እናገር ፡ ዘንድ ። መዝሙር ፡ (፸፫) ፡ ፳፰

፮) እግዚአብሔርን ፡ መጠባበቅ
 እግዚአብሔር ፡ ሆይ! መድኃኒትህን ፡ እጠብቃለሁ ። ዘፍጥረት ፡ ፵፱ ፡ ፲፰

እግዚአብሔርም ፡ የፍርድ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፣ ስለዚህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይራራላችሁ ፡ ዘንድ ፡ ይታገሣል ፤ ይምራችሁም ፡ ዘንድ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይላል ፤ እርሱን ፡ በመተማመን ፡ የሚጠባበቁ ፡ ሁሉ ፡ ብጹዓን ፡ ናቸው ። ኢሣያስ ፡ ፴ ፡ ፲፰

እኛ ፡ በመንፈስ ፡ ከዕምነት ፡ የጽድቅን ፡ ተስፋ ፡ እንጠባበቃለንና ። ገላትያ ፡ ፭ ፡ ፭

ወገባችሁ ፡ የታጠቀ ፡ መብራታችሁም ፡ የበራ ፡ ይሁን ፤ እናንተም ፡ ጌታቸው ፡ መጥቶ ፡ ደጁን ፡ ሲያንኳኳ ፡ ወዲያው ፡ እንዲከፍቱለት ፡ ከሠርግ ፡ እስኪመለስ ፡ ድረስ ፡ የሚጠብቁ ፡ ሰዎችን ፡ ምሰሉ ፤ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው ፡ እነዚያ ፡ ባሪያዎች ፡ ብጹዓን ፡ ናቸው ፤ ዕውነት ፡ እላችኋለሁ ፤ ታጥቆ ፡ በማዕድ ፡ ያስቀምጣቸዋል ፤ ቀርቦም ፡ ያገለግላቸዋል ። ሉቃስ ፡ ፲፪ ፡ ፴፭ _ ፴፯


እግዚአብሔር አምላክህ አብዝተቹ ይባርካቹ በኃጥኃትህ ብዛት የተነስ እግዚአብሔር መደን ለማየት አልቻልኩም እግዚአብሔር በምህርቱ እንደያግዝልኝ ፀልውልኝ ወገኖች