ነገርን ፡ ሁሉ ፡ በጊዜው (Negeren Hulu Begiziew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ሚስጥረኛዬ
ሁለንተናዬን ፡ ዳሰሰው ፡ ዛሬ ፡ ገባ ፡ ከጓዳዬ
የሌለኝ ፡ ከእጄ ፡ ለጠፋ ፡ በቤቴ ፡ ውስጥ ፡ ለጐደለው
ሁሉም ፡ በጊዜው ፡ ሲሞላ ፡ ኢየሱስ ፡ ውብ ፡ አደረገው

አዝ፦ ነገርን ፡ ሁሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፪x) ፡ ሰራው ፡ ጌታዬ
የጥንት ፡ አምባ ፡ ከለላዬ ፡ የውስጤን ፡ ብሶት ፡ ችግሬን
ልዑል ፡ ቀደደልኝ ፡ ማቄን ፡ ስሙ ፡ ይክበር (፪x) ፡ ኢየሱስ
አብሶልኛል ፡ ዕንባዬን

ዓለምና ፡ ሥጋ ፡ ሰይጣን ፡ ማጣት ፡ ማግኘት ፡ ተፈራርቀው
የያዝኩትን ፡ ሊያስለቅቁኝ ፡ እምነቴን ፡ እንደ ፡ ጨው ፡ አሟምተው
የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ የችግር ፡ ገመዴን ፡ ፈታው
ምቀኛዬን ፡ አሳፈረው ፡ የጠላቴን ፡ ራስ ፡ መታ

አዝ፦ ነገርን ፡ ሁሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፪x) ፡ ሰራው ፡ ጌታዬ
የጥንት ፡ አምባ ፡ ከለላዬ ፡ የውስጤን ፡ ብሶት ፡ ችግሬን
ልዑል ፡ ቀደደልኝ ፡ ማቄን ፡ ስሙ ፡ ይክበር (፪x) ፡ ኢየሱስ
አብሶልኛል ፡ ዕንባዬን

በመጠበቂያው ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ኧረኛዬን ፡ ጠራሁት
ልዑል ፡ ፀጋው ፡ አበረታኝ ፡ የሚያየኝንም ፡ አየሁት
ችግር ፡ ጸሎቴንም ፡ ስማኝ ፡ ያስቸገረኝንም ፡ አሰረ
ይፋ ፡ ወጣ ፡ ባደባባይ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ከበረ

አዝ፦ ነገርን ፡ ሁሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፪x) ፡ ሰራው ፡ ጌታዬ
የጥንት ፡ አምባ ፡ ከለላዬ ፡ የውስጤን ፡ ብሶት ፡ ችግሬን
ልዑል ፡ ቀደደልኝ ፡ ማቄን ፡ ስሙ ፡ ይክበር (፪x) ፡ ኢየሱስ
አብሶልኛል ፡ ዕንባዬን

ችግረኛውን ፡ ከመሬት ፡ ምስኪን ፡ ከጉድፍ ፡ ያነሳል
ልዑል ፡ ግራ ፡ የተጋባ ፡ ባይተዋር ፡ ያስጠጋል
ለጥቂት ፡ ያስጨነቀኝም ፡ ቆንጆ ፡ መልካም ፡ አረገልኝ
ኢየሱስ ፡ በራሱ ፡ ዘመን ፡ አየ ፡ ጸሎቴን ፡ ሰማልኝ

አዝ፦ ነገርን ፡ ሁሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፪x) ፡ ሰራው ፡ ጌታዬ
የጥንት ፡ አምባ ፡ ከለላዬ ፡ የውስጤን ፡ ብሶት ፡ ችግሬን
ልዑል ፡ ቀደደልኝ ፡ ማቄን ፡ ስሙ ፡ ይክበር (፪x) ፡ ኢየሱስ
አብሶልኛል ፡ ዕንባዬን

ማዳን ፡ በማይችሉ ፡ ሰዎች ፡ በዓለቆች ፡ አትታመኑ
ዐይኖቻችሁን ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ወደ ፡ ፈጣሪያችሁ ፡ አቅኑ
ምንም ፡ በለስ ፡ ባታፈራ ፡ የወይራ ፡ ስር ፡ ቢጐድልም
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ኑሮ ፡ ነው ፡ የታመኑትን ፡ አይጥልም

አዝ፦ ነገርን ፡ ሁሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፪x) ፡ ሰራው ፡ ጌታዬ
የጥንት ፡ አምባ ፡ ከለላዬ ፡ የውስጤን ፡ ብሶት ፡ ችግሬን
ልዑል ፡ ቀደደልኝ ፡ ማቄን ፡ ስሙ ፡ ይክበር (፪x) ፡ ኢየሱስ
አብሶልኛል ፡ ዕንባዬን