ነፍሴን ፡ ተናገር (Nefsien Tenager)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ነፍሴን ፡ ተናገር ፡ ኢየሱስ
ቀስ ፡ ብለህ ፡ ንገረኝ
በቸርነት ፡ አስታውቀኝ
አልተውህም ፡ በለኝ
እንዳዳምጥህ ፡ ልብ ፡ ስጠኝ
ቃልህን ፡ እንድሰማ
ነፍሴ ፡ ምሥጋና ፡ ትምላ
በአንተም ፡ ደስ ፡ ይበለኝ

ልጆችህን ፡ ተናገር
መንገድህን ፡ ምራቸው
በደስታም ፡ ምላቸው
ጸሎት ፡ አስተምራቸው
ሕይወታቸውን ፡ ቀድስ
ለአንተ ፡ ሁሉን ፡ ይስጡህ
መንግሥትህን ፡ ያፋጥኑ
አንተን ፡ እስክናይህ

እንደጥንቱ ፡ ተናገር
ምኞትህ ፡ ይገለጽ
ተግባሬን ፡ ሁሉ ፡ ልወቅ
ፈቅድህን ፡ ልፈጽም
ምራኝ ፡ አከብርህም ፡ ዘንድ
ክብርህን ፡ እንዳይ
በደስታ ፡ እንድታዘዝ
ሰርክም ፡ እንዳከብርህ