ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ (Nefsien Befiteh Afesalehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬ ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግሻለሁ
(፪x)

ሊታይ ፡ በማይችል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ አለህ
ሰማይ ፡ ምድርን ፡ በቃል ፡ ታዛለህ
ወደም ፡ ጠላም ፡ ፍጥርት ፡ በሙሉ
ይገዛልሃል ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ኃይሉ

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬ ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግሻለሁ
(፪x)

ሰው ፡ ህልውናው ፡ ሞትና ፡ ሕይወቱ
ሃዘን ፡ ደስታው ፡ ሹመት ፡ ሽረቱ
ትዕዛዝ ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ ይወጣል
ክብር ፡ ላንተ ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይሰጣል

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬ ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግሻለሁ
(፪x)

እስከ ፡ እግርህ ፡ ጣት ፡ ዕንቁ ፡ ለብሰሃል
ወገብህንም ፡ በወርቅ ፡ ታጥቀሃል
ራሽ ፡ ነጭ ፡ ነው ፡ ዐይንህ ፡ ነበልባል
ክብርም ፡ ስግደትም ፡ ለአንተ ፡ ይገባሃል

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬ ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግሻለሁ
(፪x)

እግርህ ፡ በእቶን ፡ የነጠረ ፡ ናስ
ድምጽህ ፡ ያስፈራል ፡ እንደውቅያኖስ
የተሳለ ፡ ሰይፍ ፡ ከአፍህ ፡ ይወጣል
ከቀትር ፡ ፀሐይ ፡ ይልቅ: ፊትህ ፡ ያበራል

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬ ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግሻለሁ
(፪x)

ውለታህ ፡ በዝቶ ፡ ቢያስጨንቀኝ
ያለኝን ፡ ሸጬ ፡ ሽቶ ፡ ገዛሁልህ
ብልቃጡ ፡ ይሰበር ፡ ይፍሰስ ፡ በእግርህ
እንዳከበርከኝ ፡ እኔም ፡ ላክብርህ

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬ ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግሻለሁ
(፪x)