ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዕረጊ (Nefsie Hoy Eregi)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ወደ ፡ ቅዱስ ፡ ቁስሉ
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዕረጊ!
ወደ ፡ ረጅም ፡ መስቀሉ
አምነሽ ፡ ተጠጊ
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ እረኛሽም
ሞተ ፡ ለበጐቹ
ዕዳን ፡ ሁሉ ፡ ከፈለም
ስለ ፡ ወንድሞቹ

ከአምላክ ፡ ፍርድ ፡ ሊጋርደን
ወርቅም ፡ ብርም ፡ ሆነ
ከጥፋት ፡ ሊያድነን
የማይበቃ ፡ ሆነ
ነገር ፡ ግን ፡ የአምላክ ፡ ልጅ
መሥዋዕት ፡ ሆነ
እኛንም ፡ ከሰይጣን ፡ እጅ
በሕማሙ ፡ አዳነን

በሕማሙም ፡ ካመንሁ
በእርሱ ፡ እድናለሁ
ጽድቁን ፡ ከተቀበልሁ
ጻድቅ ፡ እሆናለሁ
ንጹህ ፡ ደሙን ፡ አፍስሶ
የአምላክ ፡ በግ ፡ ሞተልኝ
ኃጢአቴን ፡ ደምስሶ
ቅዱስ ፡ እርድ ፡ ሆነልኝ

ደሙም ፡ ስላጸደቀኝ
ዓብ ፡ ይቀበለኛል
የልጁም ፡ ሙሽራ ፡ ነኝ
በእርሱም ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ተባበረ
የዓለም ፡ ፍትወት ፡ ይጥፋ
ኢየሱስ ፡ በእኔ ፡ ካደረ
የእርሱ ፡ ነኝ ፡ በተስፋ

ቁስሎቹ ፡ ለሰማይ
ቡሩካን ፡ ደጆች ፡ ናቸው
ችጋረኞች ፡ ወደ ፡ ላይ
ክፍት ፡ በር ፡ አላቸው
ለሚታመመውም ፡ ደሃ
ጠበሉ ፡ መነጨ
ቅዱስ ፡ የሕይወት ፡ ውሃ
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ተረጨ

ወደ ፡ ቅዱስ ፡ ቁስሉ
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዕረጊ!
ጤናሽ ፡ ነው ፡ በመስቀሉ
ከእርሱ ፡ አትራቂ!
በዚህ ፡ ቅዱስ ፡ አምባ ፡ ላይ
ሕይወት ፡ ታገኛለሽ
ከፍርሃትና ፡ ሥቃይ
በእርሱ ፡ ትድኛለሽ