ነፍሴ ፡ ደስ ፡ የምትሰኝብህ ፡ ጌታ (Nefsie Des Yemetesegnebeh Gieta)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ነፍሴ ፡ ደስ ፡ የምትሰኝብህ ፡ ጌታ
በጭንቀቴ ፡ የምጠራህ ፡ አጽናኝ ፡ ደጋፊ
ብርቱ ፡ መከታዬ
ተስፋዬ ፡ ሁለንተናዬ
ግሩም ፡ ጣፋጭ ፡ የሆነው ፡ ቃሉ
ኃይልም ፡ በሞት ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ይዘልቃል
በፊቱ ፡ ሁሉንም ፡ ያንበረክካል
የሕይወት ፡ ሽታው ፡ ይደርሳል
ከአፉም ፡ የጽድቅ ፡ ነገር ፡ ይመነጫል
የፀጋን ፡ ተክል ፡ ያጠጣል
አሕዛብ ፡ መዳናቸውን ፡ ያውቁበታል
በፊቱም ፡ ደስ ፡ ይሰኛሉ
በማዳኑ ፡ ሁሉም ፡ ይደሰታሉ
መላዕክት ፡ ይዘምራሉ
ሠራዊትም ፡ ሁሉ ፡ ይታዘዙታል
ለዘለዓለምም ፡ ከፍ ፡ ይላል
|