ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አለች (Nefsie Anten Alech)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከምድረበዳው ፡ ኑሮ ፡ ከዚያ ፡ ከቃጠሎ
አንተ ፡ ነህ ፡ የታደግሃት ፡ ደረስክላት ፡ ቶሎ
ስለዚህም ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች
ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ፊትህን ፡ ፈለገች

አዝ፦ ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፊሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)

ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለነፍሴ ፡ ትርጉሟ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ የኑሮ ፡ ጣዕሟ
ያላንተ ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አይሆንላትም
መጠጊያ ፡ ጐጆሌላ ፡ የላትም

አዝ፦ ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፊሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)

ባስለመድከኝ ፡ ስፍራ ፡ እጠብቅሃለሁ
አንተን ፡ ካላገኘሁ ፡ መቼ ፡ እተኛለሁ
ሌሊት ፡ ጭር ፡ ብሏል ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ተኝቷል
ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆኑን ፡ ነፍሴ ፡ ግን ፡ አምሯታል

አዝ፦ ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፊሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)

እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ እመካበታለሁኝ
እስከዘለዓለሙ ፡ ተስፋ ፡ አደርጋለሁኝ
ምንም ፡ ሳትሰራልህ ፡ ነፊሴን ፡ ወደሃታል
ለቀሪውስ ፡ ጉዞ ፡ ምንድን ፡ ያሰጋታል

አዝ፦ ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፊሴ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች (፬x)