ነቢያት ፡ ያዩልን ፡ ቀን (Nebiyat Yayulen Qen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ነቢያት ፡ ያዩልን ፡ ቀን
አሁን ፡ ጐሕ ፡ ወጣልን
አምላክ ፡ ከወረደልን
በፍቅሩ ፡ ደስ ፡ ይበለን

አዝ፦ ሆሣዕና ፡ ስግደት ፡ ክብረት
አሁን ፡ እናቅርብለት

ዘውድ ፡ አልተቀዳጀም
እንደርሱ ፡ ግን ፡ የለም
ጌጡ ፡ አይታይ ፡ ለዓለም
ሞትን ፡ ግን ፡ ሊያወድም

አዝ፦ ሆሣዕና ፡ ስግደት ፡ ክብረት
አሁን ፡ እናቅርብለት

ሳለ ፡ ጠቅላይ ፡ ንጉሥ
ሆነ ፡ ትሑት ፡ ዕጉሥ
በርኅራሄ ፡ ነው ፡ ውዱስ
በፍርዱም ፡ ጻድቅ ፡ ቅዱስ

አዝ፦ ሆሣዕና ፡ ስግደት ፡ ክብረት
አሁን ፡ እናቅርብለት

ይህን ፡ ንጉሥ ፡ ጥራ
ወደ ፡ ልብህ ፡ አግባ
ከአንተ ፡ ኪዳን ፡ ሊጋባ
ቤትህ ፡ ደስታ ፡ ሊመላ

አዝ፦ ሆሣዕና ፡ ስግደት ፡ ክብረት
አሁን ፡ እናቅርብለት