ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ (Na Gietayie Gieta Hoy)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ህዝብህ ፡ ይጠብቅሃል ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
መገለጥህ ፡ ናፍቆታል ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
እባክህ ፡ ናልኝ ፡ ሳትቆይ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ

አዝና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ

ድካሙ ፡ ሳይበረታ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
አርበኛው ፡ ሳይረታ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
የተጋዳዩ ፡ አለኝታ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
በጠላትህ ፡ ላይ ፡ በረታ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ

አዝና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ

ስምህን ፡ ስለወደደች ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ነፍሴ ፡ ስድብ ፡ ጠገበች ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ባርኮቷን ፡ እያሰበች ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ዛሬም ፡ በአንተ ፡ ታምናለች ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ

አዝና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ

ጣዖቱ ፡ ተሰባብሮ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ልመልከት ፡ ስምህ ፡ ከብሮ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ከጥንት ፡ እንደታወቅህ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ምድር ፡ አንተን ፡ ትወቅህ ፡ ና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ

አዝና ፡ ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፫x)
ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ