ና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤን ፡ አሙቀው (Na Gieta Eyesus Lebien Amuqew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ልቤን ፡ አሙቀው
የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ጣዖትን ፡ አርቀው
በውስጤም ፡ ንገሥ ፡ ኃጢአቴን ፡ ፋቀው
ና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ኦ ፡ ቸር ፡ ወዳጄ ፡ መንፈሴን ፡ ጐብኘው
አንተ ፡ ነህ ፡ ረጂዬ ፡ ደስ ፡ የምታሰኘው
ፀጋህን ፡ ከእጅህ ፡ አሁን ፡ እንዳገኘው
ና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ና ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ ፡ በኃዘን ፡ ሁሉ
ፍርሃት ፡ ሲይዘኝ ፡ ጭንቀትም ፡ ምሉ
ና ፡ ጌታ ፡ አድነኝ ፡ ከሚጐዳኝ ፡ ሁሉ
ና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ኢየሱስ ፡ ሲመጣ ፡ በማይወሰን ፡ ክብር
ልቡ ፡ የነጻ ፡ ቢያገኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
በቶሎ ፡ ይምጣ ፡ ይቅረብ ፡ በፍቅር
ና ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ