መጣሁ ፡ ወደመስቀልህ (Metahu Wedemesqeleh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

መጣሁ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ
ምስኪን ፡ ነኝ ፡ ደካማም ፡ ነኝ
ወደ ፡ አንተ ፡ እንድቀርብ
ኦ ፡ መድሃኒቴ ፡ እርዳኝ

አዝ፦ በአንተ ፡ አምናለሁኝ
ብሩክ ፡ የቀራኒዮ ፡ በግ
ተንበርክኬ ፡ በጸሎት
አድነኝ ፡ ኢኢየሱስ ፡ አድነኝ

ያለኝንም ፡ ሰጠሁህ
የምድር ፡ መዝገቤንም
ሥጋና ፡ ነፍስ ፡ ለአንተ ፡ ሊሆን
ለዘለዓለም ፡ ሁሉን ፡ ለአንተ

አዝ፦ በአንተ ፡ አምናለሁኝ
ብሩክ ፡ የቀራኒዮ ፡ በግ
ተንበርክኬ ፡ በጸሎት
አድነኝ ፡ ኢኢየሱስ ፡ አድነኝ

በተስፋህም ፡ አምናለሁ
እርዳኝ ፡ ኦ ፡ የአምላክ ፡ በግ
በምድር ፡ ጭንቀት ፡ አለሁ
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

አዝ፦ በአንተ ፡ አምናለሁኝ
ብሩክ ፡ የቀራኒዮ ፡ በግ
ተንበርክኬ ፡ በጸሎት
አድነኝ ፡ ኢኢየሱስ ፡ አድነኝ

ኢየሱስ ፡ ነፍሴን ፡ አዳናት
በእርሱ ፡ የጸናሁኝ ፡ ነኝ
እኔ ፡ በእርሱ ፡ ድኛለሁ
ለበጉ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን

አዝ፦ በአንተ ፡ አምናለሁኝ
ብሩክ ፡ የቀራኒዮ ፡ በግ
ተንበርክኬ ፡ በጸሎት
አድነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አድነኝ