ምስጢሬን ፡ ለሚያውቀው ፡ ጌታ (Mestirien Lemiyawqew Gieta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ተስፋ ፡ ያደረኩት ፡ ፈጽሞ ፡ ሲጠፋ
እጅግም ፡ ስከፋ ፡ ለአምላኬ ፡ እነግረዋለሁ
በፊቱም ፡ አነባለሁ
መቼም ፡ ያለኝ ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ምስጢሬን ፡ ለሚያውቀው ፡ ለጌታ
እነግረዋለሁኝ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
በሬን ፡ ዘግቼ ፡ ከኋላዬ
ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ በጓዳዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ችግሬን ፡ በእንባ ፡ አዋየዋለሁ

ሁሉ ፡ ሲሞላማ ፡ ማን ፡ ይጠፋል ፡ ከደጅ
ጠላት ፡ ቢሆን ፡ ወዳጅ
ያለውን ፡ ከእጅ ፡ ሲያጡ
ሲነጡ ፡ ሲገረጡ
ያኔ ፡ ጭር ፡ ይላል ፡ ቤቱ ፡ ጭር ፡ ይላል

አዝ፦ ምስጢሬን ፡ ለሚያውቀው ፡ ለጌታ
እነግረዋለሁኝ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
በሬን ፡ ዘግቼ ፡ ከኋላዬ
ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ በጓዳዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ችግሬን ፡ በእንባ ፡ አዋየዋለሁ

ሁሌ ፡ ደልቶኝ ፡ አይደል ፡ ጌታን ፡ የማመልከው
ተመስገን ፡ የምለው
በማጣት ፡ በማግኘቴ
በደስታም ፡ በሐዘኔ
ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ከጐኔ (፪x)

አዝ፦ ምስጢሬን ፡ ለሚያውቀው ፡ ለጌታ
እነግረዋለሁኝ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
በሬን ፡ ዘግቼ ፡ ከኋላዬ
ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ በጓዳዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ችግሬን ፡ በእንባ ፡ አዋየዋለሁ

ፊት ፡ አይቶ ፡ የማይደፈርድ ፡ የልብ ፡ የሚረዳ
የሚያውቅ ፡ የጓዳ ፡ ብከሳ ፡ ወይ ፡ ብጠቁር
ብደኸይ ፡ ወይ ፡ ብከብር
አይተወኝም ፡ እግዚአብሔር (፪x)

አዝ፦ ምስጢሬን ፡ ለሚያውቀው ፡ ለጌታ
እነግረዋለሁኝ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
በሬን ፡ ዘግቼ ፡ ከኋላዬ
ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ በጓዳዬ
የልቤን ፡ አጫውተዋለሁ
ችግሬን ፡ በእንባ ፡ አዋየዋለሁ