ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ ፡ ጌታ (Mesganayie Wede Ante Yedres Gieta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከምናምንቴ ፡ ከተራ ፡ ሥፍራ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ
ሰው ፡ ልታደርገኝ ፡ እኔን ፡ የጠራህ ፡ ዝማሬዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ
አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ከቶ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ፡ እስከዚህ ፡ ድረስ ፡ ከፍ ፡ ያደረከኝ
ክብርህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ተገልጿልና ፡ ከአንደበቴ ፡ ይኸው ፡ ምሥጋና

አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ ፡ ጌታ

ከታላላቆች ፡ ከከበሩት ፡ ጋር ፡ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ
ትልቅ ፡ ተብዬ ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር ፡ ዝማሬዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ
በጠላቴ ፡ ፊት ፡ ዘይት ፡ ቀብተህ ፡ አቁመኸኛል ፡ ሕያው ፡ አድርገህ
በተቀደሰ ፡ በነጻ ፡ አንደበት ፡ ነፍሴ ፡ ትዘምር ፡ በቀን ፡ በሌሊት

አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ ፡ ጌታ

ባማረ ፡ ሥፍራ ፡ ገመድ ፡ ወድቆልኝ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ
በአደባባይ ፡ ስምህን ፡ እጠራለሁኝ ፡ ዝማሬዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ
ታሪክ ፡ የምትለውጥ ፡ የምታስገርም ፡ ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ አንደአንተ ፡ የለም
ክበር ፡ ልበልህ ፡ ንገሥ ፡ ልበልህ ፡ በሰማይ ፡ በምድር ፡ አምሣያ ፡ የሌለህ

አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ ፡ ጌታ

ከጠራሃቸው ፡ ከሕዝብህ ፡ ጋራ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ ፡ ጌታ
ስለታደምኩኝ ፡ እራት ፡ ልበላ ፡ ዝማሬዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ ፡ ጌታ
ተምለው ፡ አጣሁ ፡ የምመልሰው ፡ ስለውለታህ ፡ ለአንተ ፡ የምሰጠው
የጌቶች ፡ ጌታ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ስምህ ፡ ይባረክ

አዝ፦ ምሥጋናዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ይድረስ ፡ ጌታ