ምሥጋናዬ (Mesganayie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ ሌጌታዬ ፡ ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ በዜማዬ ፡ ምሥጋናዬ

ኮብልዬ ፡ የጠፋሁ ፡ ሳለሁ ፡ በደለኛ
በፍቅር ፡ መልሰህ ፡ አረከኝ ፡ ጓደኛ
የሃሳብህ ፡ ተካፋይ ፡ የቅርብ ፡ ምስጢረኛ
በማዕድን ፡ ዙሪያ ፡ አገልጋይ ፡ ቤተኛ (፫x)

አዝምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ ሌጌታዬ ፡ ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ በዜማዬ ፡ ምሥጋናዬ

የቅርብ ፡ ወዳጆቹ ፡ ለንግስ ፡ ሲጠብቁት
ተስማምቶ ፡ ተገኘ ፡ በመስቀል ፡ ለመሞት
እስትንፋስ ፡ ያላችሁ ፡ ጌታን ፡ አመስግኑ
እኛን ፡ ላመታደግ ፡ ጸንቷል ፡ በኪዳኑ (፫x)

አዝምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ ሌጌታዬ ፡ ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ በዜማዬ ፡ ምሥጋናዬ

የሥጋ ፡ ባህሪ ፡ አጥብቆ ፡ ታገለው
እንደ ፡ ደም ፡ ነጠብጣብ ፡ ላብ ፡ እስኪያልበው
ሄደ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ አለ ፡ ተፈጸመ
ባፈሰሰው ፡ ደሙ ፡ የእርቅ ፡ ውል ፡ ታተመ (፫x)

አዝምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ ሌጌታዬ ፡ ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ በዜማዬ ፡ ምሥጋናዬ

ወንድሜ ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ እህቴም ፡ እንዲሁ
የውሆች ፡ ፈጣሪ ፡ ያለ ፡ ተጠማሁ
አምነን ፡ እንዳን ፡ ከኃጢአት ፡ በሽታ
ምህረት ፡ የሚያበቃበት ፡ ያቺ ፡ ቀን ፡ ሳትመጣ (፫x)

አዝምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ ሌጌታዬ ፡ ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ (፪x) ፡ ይኸው ፡ በዜማዬ ፡ ምሥጋናዬ