ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና (Mesgana Zariem Mesgana)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ነገም ፡ ምሥጋና
እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛ ፡ ስመ ፡ ገናና
እንቀኝልሃለን ፡ እንዘምርልሃለን
ሌላ ፡ ምን ፡ ድርሻ ፡ አለንና

የዚህ ፡ ዓለም ፡ ክፉ ፡ በስሩ ፡ አርጐ ፡ ሲያንገላታን
ከምድር ፡ ጉስቁልና ፡ ሐዘን ፡ ቅዱስ ፡ ስምህ ፡ ስለፈታን
ነጻነት ፡ ስላገኘን ፡ ከእኛ ፡ ወድቆ ፡ ቀንበራችን
ባለፈው ፡ መርካት ፡ አልቻልንም ፡ ዛሬም ፡ ይኸው ፡ ምሥጋናችን

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ነገም ፡ ምሥጋና
እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛ ፡ ስመ ፡ ገናና
እንቀኝልሃለን ፡ እንዘምርልሃለን
ሌላ ፡ ምን ፡ ድርሻ ፡ አለንና

በየቀኑ ፡ በላያችን ፡ ከሚሰነዘረው ፡ ጥቃት
ምሽግ ፡ ሆነህ ፡ መጠለያ ፡ አድነኸናል ፡ ከጥፋት
እኛን ፡ የሚያስመካን ፡ ጌታ ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ስለሌለን
ደግመን ፡ ደጋግመን ፡ ለስምህ ፡ ስግደትን ፡ እናቀርባለን

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ነገም ፡ ምሥጋና
እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛ ፡ ስመ ፡ ገናና
እንቀኝልሃለን ፡ እንዘምርልሃለን
ሌላ ፡ ምን ፡ ድርሻ ፡ አለንና

ፍላጻውን ፡ አነጣጥሮ ፡ ቢወነጨፍ ፡ በላያችን
ክንድ ፡ ብርቱ ፡ ስለሆነ ፡ ጌታ ፡ የጦር ፡ አዝማቻችን
አንተን ፡ አልፎ ፡ መች ፡ ሊነካን ፡ እንዲያው ፡ ማስፈራራት ፡ እንጂ
እረፍትን ፡ ተለማምደናል ፡ ተመክተን ፡ በአንተ ፡ እጅ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ነገም ፡ ምሥጋና
እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛ ፡ ስመ ፡ ገናና
እንቀኝልሃለን ፡ እንዘምርልሃለን
ሌላ ፡ ምን ፡ ድርሻ ፡ አለንና

ዕለት ፡ ዕለት ፡ ከሚከበን ፡ ከኃጢአት ፡ ወጥመድ ፡ አስጥለኸን
በቅዱስ ፡ ደምህ ፡ ቀድሰህ ፡ የአንተ ፡ ገንዘብ ፡ ስላረከን
ደግመን ፡ እንባርክሃለን ፡ በምሥጋና ፡ ተሞልተናል
መጽናናትና ፡ በረከት ፡ ደስታ ፡ በአንተ ፡ ሆኖልናል

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ምሥጋና ፡ ነገም ፡ ምሥጋና
እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛ ፡ ስመ ፡ ገናና
እንቀኝልሃለን ፡ እንዘምርልሃለን
ሌላ ፡ ምን ፡ ድርሻ ፡ አለንና