ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (Mesgana Temoltalech Nefsie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

ተረስቻለሁ ፡ ጌታ ፡ ትቶኛል
የተጣልኩኝ ፡ ነኝ ፡ ማን ፡ ያስበኛል
ብዬ ፡ ሳነባ ፡ የራራህልኝ
ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላስታወስከኝ

አዝምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

ቤት ፡ የሌላት ፡ ወፍ ፡ ሆኜ ፡ ከርታታ
ያደላደልከኝ ፡ የእረፍት ፡ ጌታ
ለልቤ ፡ ትምክህት ፡ ስለሆንክልኝ
ከፍ ፡ በል ፡ ውዱ ፡ አምላኬ ፡ ስላከበርከኝ

አዝምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

ባዶ ፡ ሕይወቴን ፡ በዘይት ፡ ሞልተህ
ጥማቴን ፡ ሁሉ ፡ ከጅህ ፡ አርክተህ
በፍቅርህ ፡ ስበህ ፡ ሰው ፡ ስላረከኝ
ተመስገን ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ስላከበርከኝ

አዝምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

አንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሁሌ ፡ በምክርህ
ሰው ፡ እንዳይጠፋ ፡ ነውና ፡ ሃሳብህ
በሕይወት ፡ ቃልህ ፡ ልቤን ፡ አቀናህ
ከፍ ፡ በል ፡ በምድር ፡ ይግነን ፡ ክብርና ፡ ዝናህ

አዝምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x)
አቀርብሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ