ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ (Mesgana New Yalegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታ (፪x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ ልከፍለው

በወደኩኝ ፡ ጊዜ ፡ ድካሜን ፡ ተረድቶ
ደግፎ ፡ የሚያነሳኝ ፡ ዳግም ፡ በኃይሉ ፡ ሞልቶ
ለሕይወቴ ፡ ረዳት ፡ ለነፍሴ ፡ መጽናኛ
ከጌታዬ ፡ በቀር ፡ ማን ፡ አለኝ ፡ ጓደኛ

አዝምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታ (፪x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ ልከፍለው

መንገዴ ፡ ጨለማ ፡ ፅልመት ፡ ሲያለብሰው
የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ሳለሁ
ለመንገዴ ፡ መብራት ፡ ሆኖ ፡ ለእግሬ ፡ ብርሃን
ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ ሊያሳየኝ ፡ መንገዱን

አዝምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታ (፪x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ ልከፍለው

ብቸገር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አብሮኝ ፡ ተኮራምቶ
ሳዝን ፡ ተስፋ ፡ ስቆርጥ ፡ ሲከፋኝ ፡ አጽናንቶ
እንደ ፡ እርሱ ፡ ተሰምቶት ፡ ችግሬን ፡ ተረድቶ
ለልቤ ፡ የሚደርስ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ከሰው ፡ ከቶ

አዝምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታ (፪x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ ልከፍለው

የመከራን ፡ ጽዋ ፡ ብቻዬን ፡ ስጠጣ
የልቤ ፡ የሚገባው ፡ የማዋየው ፡ ሳጣ
በሐዘኔ ፡ ብዛት ፡ ማጉረምረም ፡ ስቃጣ
ይታየኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሲመጣ

አዝምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታ (፪x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ ልከፍለው