From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ በዕልልታ (፪x) በሽብሸባ (፪x)
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ
እጅግ ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ የከበረ
ስሙም ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ የነበረ
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነውና
ልግባ ፡ ለአምላኬ ፡ ልስጥ ፡ ምሥጋና
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ በዕልልታ (፪x) በሽብሸባ (፪x)
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ
ምርኮኛ ፡ የነበርኩ ፡ ለጠላት
ባለ ፡ እግርና ፡ ባለ ፡ እጅ ፡ ሰንሰለት
ዛሬ ፡ ግን ፡ የታል ፡ ተበጣጥሷል
የሞት ፡ ድምጽ ፡ ከእኔ ፡ ተወግዷል
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ በዕልልታ (፪x) በሽብሸባ (፪x)
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ
እጅግ ፡ ወደአማረ ፡ ማደሪያው
ብዙ ፡ በረከት ፡ ወደሚያፈሰው
እንድገባ ፡ ወዶኛልና
ልስገድለት ፡ ልቀኝ ፡ በደስታ ፡ ዜማ
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ በዕልልታ (፪x) በሽብሸባ (፪x)
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ
ውርደቴን ፡ በክብር ፡ ለውጧል
ሸክሜን ፡ ከላዬ ፡ ላይ ፡ አንስቷል
ለምን ፡ እሆናለሁ ፡ እንዳልተፈታ
እስኪ ፡ ላዚምለት ፡ በዕልልታ
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ በዕልልታ (፪x) በሽብሸባ (፪x)
ይዤ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ልግባ
ይዤ ፡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ልግባ
|