ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ላቅርብ ፡ ለጌታዬ (Mesgana Mesgana Laqreb Legietayie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በዚች ፡ በዕድሜ ፡ ዘመን ፡ ስኖር ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር
ብዙ ፡ የሚያስደስት ፡ የሚያሳዝን ፡ ነገር
አየሁ ፡ በዐይኖቼ ፡ በጆሮቼም ፡ ሰማሁ
በፀጋው ፡ አቁሞኝ ፡ ዕድል ፡ ስላገኘሁ

አዝምሥጋና ፡ ምሥጋና (፪x)
ላቅርብ ፡ ለጌታዬ ፡ እንደገና

ሕይወት ፡ ለዛ ፡ አጥቶ ፡ ዓለም ፡ ስትከፋፋ
ክህደት ፡ ተንሰራፍቶ ፡ አምላክ ፡ ባይ ፡ ሲጠፋ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ለማለት ፡ ላበቃኝ
ምሥጋና ፡ ውዳሴ ፡ ይድረስ ፡ እላለሁኝ

አዝምሥጋና ፡ ምሥጋና (፪x)
ላቅርብ ፡ ለጌታዬ ፡ እንደገና

ያለፈውን ፡ ዘመን ፡ በደሃና ፡ አሳልፎ
ለሚመጣው ፡ ደግሞ ፡ በክንዱ ፡ ደግፎ
የሚያቆመኝ ፡ ወዳጁ ፡ ጓደኛ ፡ ስላለኝ
ምሥጋና ፡ ማቅረቡ ፡ እንዴት ፡ ይነስብኝ

አዝምሥጋና ፡ ምሥጋና (፪x)
ላቅርብ ፡ ለጌታዬ ፡ እንደገና