ምሥጋና ፡ ለአምላክ (Mesgana Lamlak)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ምሥጋና ፡ ለአምላክ ፡ ኃያሉ ፡ የፍጥረታት ፡ ንጉሥ
አወድሱት ፡ ፈቃር ፡ ነውና ፡ ቸርና ፡ ቅዱስ
የምትሰሙ ፡ ወደ ፡ መቅደስ ፡ ቅረቡ
ምሥጋና ፡ በደስታ ፡ ስጡ

አዝ፦ ማን ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳነኝ?
ምን ፡ ሠራልኝ?
ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ለአንተ ፡ ሞተ
የት ፡ ይኖራል? በሰማይ ፡ ያማልዳል
እመን ፡ አሁን ፡ በሰማይ ፡ ያማልዳል
ወደ ፡ አብ ፡ እንድረስ
ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ

ምሥጋና ፡ ለአምላክ ፡ ሁሉን ፡ በጥበብ ፡ ለሚገዛ
በክንፉ ፡ ሥር ፡ ይጋርድሃል ፡ እንዳትጐዳ
በምሕረቱ ፡ የለመንኸውን ፡ ሁሉ
ፀሎትህን ፡ ሰምቶ ፡ ይሰጣል

አዝ፦ ማን ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳነኝ?
ምን ፡ ሠራልኝ?
ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ለአንተ ፡ ሞተ
የት ፡ ይኖራል? በሰማይ ፡ ያማልዳል
እመን ፡ አሁን ፡ በሰማይ ፡ ያማልዳል
ወደ ፡ አብ ፡ እንድረስ
ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ

ምሥጋና ፡ ለአምላክ ፡ ኑሮህን ፡ ለሚያበለጽግ
ቸርነቱና ፡ ምሕረቱ ፡ ለአንተ ፡ የማያቋርጥ
ይምርሃል ፡ ጸጋውን ፡ ያለብስሃል
አሜን ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም

አዝ፦ ማን ፡ ነው ፡ ከጥፋት ፡ ያዳነኝ?
ምን ፡ ሠራልኝ?
ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ለአንተ ፡ ሞተ
የት ፡ ይኖራል? በሰማይ ፡ ያማልዳል
እመን ፡ አሁን ፡ በሰማይ ፡ ያማልዳል
ወደ ፡ አብ ፡ እንድረስ
ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረስ