From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
በበረሃ ፡ ስለእኛ ፡ ተንገላታ ፡ በረሃብ
ተጨነቀ ፡ አላበው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ የደም ፡ ላብ
ለእኛ ፡ ብሎ ፡ የሞተልን ፡ ጌታ ፡ ይባረክ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለአዳኙ ፡ ጌታ ፡ ለሥሙ ፡ ይንበርከክ
አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
ሰማይ ፡ ሰማያትን ፡ ትቶ ፡ ለወረደው
የክብር ፡ ዙፋን ፡ ለሰው ፡ ሲል ፡ የተወው
ውዳሴ ፡ ይገባዋል ፡ ጌታችን ፡ ይመስገን
በሞቱ ፡ የሞትን ፡ ሞት ፡ ሽሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያዳነን
አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
መድኃኒት ፡ ከሕያው ፡ እግዚአብሔር ፡ ተሰጠን
አዳኛችን ፡ ፈዋሻችን ፡ ጌታ ፡ ይመስገን
ከዘለዓለም ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ የእኛ ፡ አምላክ
መመኪያና ፡ አለኝታ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ይባረክ
አዝ፦ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ በልቤ
|