መሠረቴ ፡ ጠብቆ (Meserete Tebqo)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መሠረቴ ፡ ጠብቆ ፡ ብጓዝ ፡ እወዳለሁ
ያለዚያ ፡ በነፋስ ፡ እወዛወዛለሁ
እንደ ፡ እኔማ ፡ እንደ ፡ ሃሣቤ
ድል ፡ ተሞልቶ ፡ ባየሁ ፡ ልቤ

አዝ ፣
እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጥዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ

ማጉረምረምም ፡ ጠፍቶ ፡ ምሥጋና ፡ ዘላለም
በደስታ ፡ ሰሞን ፡ በሥቃይ ፡ ብሆንም
ይህን ፡ ነበር ፡ የምመኘው
ውጊያ ፡ በዝቶ ፡ የት ፡ ላግኘው?

አዝ ፣
እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጥዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ

መብራቴ ፡ እየበራ ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ ፡ ኢየሱስ
ንጹሕ ፡ ቦታ ፡ አግኝቶ ፡ ቢኖር ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ
ይህን ፡ ነበር ፡ የምመኘው
ውጊያ ፡ በዛ ፡ የት ፡ ላግኘው?

አዝ ፣
እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጥዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ

ቅድስና ፡ ሞልቶባቸው ፡ ሁሉም ፡ ብልቶቼ
በኑሮዬ ፡ በጌታ ፡ ክንድ ፡ ሥጋዬን ፡ ገዝቼ
ልኖር ፡ ነበር ፡ የምመኘው
ውጊያ ፡ በዝቶ ፡ የት ፡ ላግኘው?

አዝ ፣
እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡ ልበረታ
ምኞቴ ፡ ነው ፡ ጥዋት ፡ ማታ
ለጥሞና ፡ ጊዜ ፡ አጣሁኝ
ዘወትር ፡ በውጊያ ፡ ላይ ፡ እያለሁኝ