ምራን ፡ እረኛችን (Meran Eregnachen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ትርጉም ፡ ያለው ፡ ኑሮ ፡ መኖር ፡ አስተምረን
የሰላሙን ፡ ንጉሥ ፡ ንገሥ ፡ በሕይወታችን

አዝ፦ ምራን ፡ እረኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ ተስፋችን
ፀንተን ፡ እስከምንደርስ ፡ በሰማይ ፡ ቤታችን (፪x)

ውዱ ፡ አምላካችን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መሪያችን
ጥበቃህ ፡ አይለየን ፡ ሲዝል ፡ ጉልበታችን

አዝ፦ ምራን ፡ እረኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ ተስፋችን
ፀንተን ፡ እስከምንደርስ ፡ በሰማይ ፡ ቤታችን (፪x)

ስንፈራ ፡ ስንደክም ፡ ስንተክዝ ፡ ስናዝን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ በመንፈስህ ፡ አበርታን ፡ አጽናናን

አዝ፦ ምራን ፡ እረኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ ተስፋችን
ፀንተን ፡ እስከምንደርስ ፡ በሰማይ ፡ ቤታችን (፪x)

ጠውልገን ፡ እንዳንቀር ፡ ሙላን ፡ በባርኮትህ
ዓለምልመን ፡ በፀጋህ ፡ አቁመን ፡ ለክብርህ

አዝ፦ ምራን ፡ እረኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ ተስፋችን
ፀንተን ፡ እስከምንደርስ ፡ በሰማይ ፡ ቤታችን (፪x)

ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ፈተና ፡ ሲያጠቃን
አትለየን ፡ እምባችን ፡ ኢየሱስ ፡ እረኛችን

አዝ፦ ምራን ፡ እረኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ ተስፋችን
ፀንተን ፡ እስከምንደርስ ፡ በሰማይ ፡ ቤታችን (፪x)