መንገዴን ፡ ሁሉ (Mengedien Hulu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ
ጌታ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ልጓዝ
ልሁን ፡ ከአንተ ፡ ጋር

የዘለዓለም ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ መጠጊያና ፡ አምባዬ
እስከ ፡ ፍጻሜ ፡ እሄዳለሁ ፡ አንተን ፡ ተከትዬ
መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እስከ ፡ መጨረሻ
እከተልሃለሁኝ ፡ የሕይወቴን ፡ ጋሻ

አዝ፦ መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ
ጌታ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ልጓዝ
ልሁን ፡ ከአንተ ፡ ጋር

በመከራ ፡ በስደትም ፡ በሚያስፈራ ፡ ነገር
ለአንተ ፡ ፀንቼ ፡ እቆማለሁ ፡ በሕይወት ፡ እንድኖር
የልብ ፡ ሰላምንና ፡ ደስታን ፡ ከሰጠኸኝ
ለአንተ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆም ፡ አደራ ፡ አስበኝ

አዝ፦ መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ
ጌታ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ልጓዝ
ልሁን ፡ ከአንተ ፡ ጋር

የሚያሰናክለኝ ፡ የለም ፡ ከክንፍህ ፡ ሥር ፡ ነጥቆ
ማንም ፡ ሊወስደኝ ፡ አይችልም ፡ ከእጅህ ፡ ፈልቅቆ
ሰይጣንም ፡ ከአንተ ፡ ሊነጥለኝም ፡ ቢሞክርም
ከአንተ ፡ ፍቅር ፡ ፍፁም ፡ ሊለየኝ ፡ አይችልም

አዝ፦ መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ
ጌታ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ልጓዝ
ልሁን ፡ ከአንተ ፡ ጋር

ደስታ ፡ እንደሌለኝ ፡ አውቃለሁ ፡ ከአንተ ፡ ከተለየሁ
ነገር ፡ ግን ፡ ተስፋ ፡ የሌለኝ ፡ ከርታታ ፡ እሆናለሁ
ግን ፡ እስከ ፡ ፍጻሜው ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ከተጓዝኩ
በሰማይ ፡ የደስታ ፡ ቤት ፡ እንዳለኝ ፡ አውቃለሁ

አዝ፦ መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ
ጌታ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ልጓዝ
ልሁን ፡ ከአንተ ፡ ጋር