መንገዴን ፡ አደራ (Mengedien Adera)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝመንገዴን ፡ አደራ ፡ አደራ (፪x)
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሳልፍ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ እንዳልፈራ

መሻገር ፡ ሲያቅተኝ
በበረሃ ፡ ውስጥ
ኃይልህ ፡ ይውረድብኝ ፡ ጌታ
ከመስቀልህ ፡ ሥር

አዝመንገዴን ፡ አደራ ፡ አደራ (፪x)
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሳልፍ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ እንዳልፈራ

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጠብቀኝ
አልሁን ፡ ከዳተኛ
መጥቶ ፡ ይቀስቅሰኝ ፡ ልጅህን
መንፈስህ ፡ ስተኛ

አዝመንገዴን ፡ አደራ ፡ አደራ (፪x)
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሳልፍ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ እንዳልፈራ

ሩጫዬን ፡ ልጨርስ
አክሊል ፡ እንዳገኝ
ልብሴን ፡ ቀይርልኝ ፡ ኢየሱስ
በቤትህ ፡ ልኑር

አዝመንገዴን ፡ አደራ ፡ አደራ (፪x)
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሳልፍ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ እንዳልፈራ

የድካም ፡ ዘመኔን
ስጨርስ ፡ አንድ ፡ ቀን
በከበረው ፡ ደምህ ፡ ኢየሱስ
አድርሰኝ ፡ እቤትህ

አዝመንገዴን ፡ አደራ ፡ አደራ (፪x)
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሳልፍ ፡ ጌታ
ፍፁም ፡ እንዳልፈራ