መንገደኛ ፡ መናኝ ፡ ሁኛለሁ (Mengedegna Menagn Hugnalehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

መንገደኛ ፡ መናኝ ፡ ሁኛለሁ
ሌሊት ፡ ብቻ ፡ ሌሊቱን ፡ በዚህ ፡ ልደር
ከአምላክ ፡ ሕዝብ ፡ ጋራ ፡ እጓዛለሁ
እርሱም ፡ ሲመራኝ ፡ እከተላለሁ
አታቆየኝ ፡ እቸኩላለሁ
ሌሊት ፡ ብቻ ፡ ሌሊቱን ፡ በዚህ ፡ ልደር

ፋሲካዬን ፡ ልብላ ፡ በፍጥነት
ቅዱስ ፡ ደሙ ፡ መድረኬንም ፡ ነክቷል
አገሬን ፡ ፈልጌ ፡ ከባርነት
እግሬ ፡ ተጫምቶ ፡ ልውጣ ፡ አርነት
አምላክ ፡ ጠራኝ ፡ ለደህንነት
ቅዱስ ፡ ደሙ ፡ ቅዱስ ፡ ደሙ ፡ ገዝቶኛል

በጉን ፡ በልቼ ፡ እቀምሳለሁ
የማገኘውን ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ
የኃጢአትን ፡ እርሾ ፡ ትቻለሁ
መድኃኒቴን ፡ እመለከታለሁ
በጉን ፡ በልቼ ፡ እመኛለሁ
የማገኘውን ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ

ወደ ፡ ከነዓን ፡ ዓይኔ ፡ ያያል
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ብሩህ ፡ ነው
በዚህ ፡ በጨለማ ፡ ሞት ፡ ያስፈራል
ድካሜም ፡ ወትሮ ፡ ያስወድቀኛል
ወደ ፡ አገሬ ፡ ዓይኔ ፡ ያያል
ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ብሩህ ፡ ነው

በዚህች ፡ ምድር ፡ ዕረፍት ፡ አይገኝም
ወዲያ ፡ ነው ፡ ወዲያ ፡ ነው ፡ ምኞቴ
በዚያ ፡ ሞት ፡ አያስለቅሰኝም
ድካም ፡ አይሰማኝ ፣ ጠላት ፡ አይደርስም
ኃጢአት ፡ አያስጨንቀኝም
ወዲያ ፡ ነው ፡ ወዲያ ፡ ነው ፡ ምኞቴ

ቸር ፡ እረኛዬ ፡ አትተወኝ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ወትሮ ፡ ሁን
ወደ ፡ ብፅዕናህ ፡ እስክታደርሰኝ
ለዓይኔም ፡ እስክትገለጥልኝ
ቸር ፡ እረኛዬ ፡ አትተወኝ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ወትሮ ፡ ሁን