መንገድ ፡ አብጅ ፡ ለጌታ (Menged Abej Legieta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

መንገድ ፡ አብጅ ፡ ለጌታ
ጠማማውም ፡ ይቅና
ይመጣል ፡ ወደ ፡ እኛ
የእሥራኤል ፡ ዋና
የጽድቅም ፡ ገዥ ፡ ይሆናል
ሥልጣኖቹን ፡ ይጨብጣል

አዝ፦ ከዓብ ፡ የመጣልን
እርሱን ፡ እናመስግን

ነዋሪ ፡ ንጉሥ ፡ ነው
ወደኛ ፡ የመጣ
ልብስን ፡ እናንጥፈው
ተፈጸመ ፡ ተስፋ
ቃሉ ፡ ዕውነት ፡ ነውና
ዘምሩ ፡ ሆሣዕና

አዝ፦ ከዓብ ፡ የመጣልን
እርሱን ፡ እናመስግን

ደጅህን ፡ ክፈትለት
ንጉሥህንም ፡ አግባ
ሊሰጥ ፡ ለሕዝብ ፡ ደህንነት
ለዓለሙ ፡ ተስፋ
በምድር ፡ ዙሪያ ፡ ሁሉ
እንዲህ ፡ ብለው ፡ ሊቀኙ

አዝ፦ ከዓብ ፡ የመጣልን
እርሱን ፡ እናመስግን

የሩሣሌም ፡ ተጣሰ
መቅደሱም ፡ ተፈታ
ክኅነቱም ፡ ተሻረ
ሉሉ ፡ ዘውዱ ፡ ጠፋ
የጌታ ፡ መንግሥት ፡ ገና ፡ በዓለሙ ፡ ሊገዛ

አዝ፦ ከዓብ ፡ የመጣልን
እርሱን ፡ እናመስግን