መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መሪያችን (Menfes Qedus Meriyachen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከክርስቲያን ፡ የማይርቀው
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መሪያችን
በበረሃ ፡ ስንመንን
እጃችንን ፡ ይዘህ ፡ ምራን
ስንሰማ ፡ መልካም ፡ ቃልህን
ደካሞች ፡ ደስ ፡ እንዲለን
መንፈስ ፡ ጥራኝ ፡ ና ፡ ብለህ
ስትመራኝ ፡ ልከተልህ

የታመንኸው ፡ ወዳጅ ፡ ሆይ
እርዳታህ ፡ እንዳይርቀን
ጨለማውም ፡ ሲያስፈራን
ጥርጥር ፡ እንዳይዘን
አውሎ ፡ ነፋስ ፡ ሲነሣ
እንዳይደክም ፡ ልባችን
መንፈስ ፡ ጥራኝ ፡ ና ፡ ብለህ
ስትመራኝ ፡ ልከተልህ

የሥራ ፡ ቀን ፡ ሲያበቃ
እረፍታችን ፡ ስንጠበቅ
ወደ ፡ ሰማያዊ ፡ ደስታ
ለመግባት ፡ ስንናፍቅ
የኢየሱስ ፡ ክቡር ፡ ደሙ ፡
ያነጻናል ፡ እንወቅ
መንፈስ ፡ ጥራኝ ፡ ና ፡ ብለህ
ስትመራኝ ፡ ልከተልህ