ምን ፡ ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ (Men Yezie Leqreb Befiteh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ምን ፡ ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ?
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ?
ፅድቄ ፡ የመርገም ፡ ጨርቅ ፡ ነው
ብትገልጠው ፡ ጉዴ ፡ ብዙ ፡ ነው

ትምክህቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የፅድቄ ፡ ፍሬ
መቆም ፡ አልችልም ፡ ፊትህ ፡ ደፍሬ
ጌታ ፡ የእኔን ፡ ነገር ፡ ተወት ፡ አድርግና
በምሕረትህ ፡ እየኝ ፡ ዛሬ ፡ እንደገና

አዝ፦ ምን ፡ ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ?
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ?
ፅድቄ ፡ የመርገም ፡ ጨርቅ ፡ ነው
ብትገልጠው ፡ ጉዴ ፡ ብዙ ፡ ነው

ስላልተቻለኝ ፡ ሥሜን ፡ መኖሩ
ከኃጢአት ፡ ጋራ ፡ መደራደሩ
በእኔ ፡ ምክንያት ፡ ሥምህ ፡ ተሰድቧል
ክፉ ፡ ሥራዬ ፡ ቤትህን ፡ አርክሷል

አዝ፦ ምን ፡ ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ?
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ?
ፅድቄ ፡ የመርገም ፡ ጨርቅ ፡ ነው
ብትገልጠው ፡ ጉዴ ፡ ብዙ ፡ ነው

ሥራዬ ፡ ሁሉ ፡ ዋግ ፡ የመታው ፡ ነው
ሕይወት ፡ የማይሰጥ ፡ ጣዕም ፡ የሌለው
ምን ፡ ይዤ ፡ ታዲያ ፡ ልስገድ ፡ በፊትህ?
የቱ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝህ?

አዝ፦ ምን ፡ ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ?
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ?
ፅድቄ ፡ የመርገም ፡ ጨርቅ ፡ ነው
ብትገልጠው ፡ ጉዴ ፡ ብዙ ፡ ነው

በአንደበቴ ፡ ሰውን ፡ አማለሁ
ደግሞ ፡ እንደገና ፡ እሳደባለሁ
በዚያው ፡ መልሼ ፡ እዘምራለሁ
ዕለት ፡ ዕለትም ፡ አሳዝንሃለሁ

አዝ፦ ምን ፡ ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ?
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ?
ፅድቄ ፡ የመርገም ፡ ጨርቅ ፡ ነው
ብትገልጠው ፡ ጉዴ ፡ ብዙ ፡ ነው