ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ (Men Yekefelehal Gieta Hoy)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ?
ብቻ ፡ ተመስገን ፡ እንልሃለን ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃል (፪X)

ፈቃድህ ፡ ሆኖ ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል
ከጠላትም ፡ እጅ ፡ ታድገኸናል
ዙሪያችንን ፡ ከበህ ፡ አንተ ፡ ጠበቅኸን
ጠላት ፡ አፈረ ፡ እኛ ፡ አልጠፋንም

አዝ፦ ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ?
ብቻ ፡ ተመስገን ፡ እንልሃለን ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃል (፪X)

ጠላት ፡ አደባ ፡ እኛን ፡ ሊያጠፋ
አንተም ፡ ተነሣህ ፡ የልጆችህ ፡ ተስፋ
ስምህን ፡ ጠርተን ፡ ጌታ ፡ አላሳፈረንም
ጠላት ፡ ሊያጠፋን ፡ ፍፁም ፡ አልቻለም

አዝ፦ ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ?
ብቻ ፡ ተመስገን ፡ እንልሃለን ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃል (፪X)

የጠላት ፡ ዛቻ ፡ ከንቱ ፡ ፉከራው
ልባችንን ፡ ጌታ ፡ ሲያናውጠው
ፍርሃት ፡ ከቦን ፡ ስናመነታ
ጽኑ ፡ ልጆቼ ፡ የምትለን ፡ ጌታ

አዝ፦ ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ?
ብቻ ፡ ተመስገን ፡ እንልሃለን ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃል (፪X)

ጠፉ ፡ ስንባል ፡ እንበዛለን
አንተ ፡ ስለሆንክ ፡ ጠባቂያችን
ስለ ፡ ውለታህ ፡ ምን ፡ ይከፈልሃል?
ተመስገን ፡ ብቻ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል

አዝ፦ ምን ፡ ይከፈልሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ?
ብቻ ፡ ተመስገን ፡ እንልሃለን ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃል (፪X)