ምን ፡ እንላለን (Men Enelalen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ መራራ
ሕይወት ፡ ብትሆን ፡ ግራ
ጨለማ ፡ ቢሆን ፡ ቀኑ
ቢጠፋብንም ፡ ውሉ
ተመስገን ፡ እንላለን
ድልን ፡ እናገኛለን

አዝምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ተመስገን
ምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ይበል

አንዱ ፡ ቁስላችን ፡ ሳይድን
ሌላው ፡ ሲፈነዳብን
ደግመን ፡ ስናስታምም
ቁስል ፡ በቁስል ፡ ሆነን
ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅማል
ክበር ፡ ብንል ፡ ይሻላል

አዝምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ተመስገን
ምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ይበል

የያዝነው ፡ ሲወድቅብን
ያፈስነው ፡ ሲፈስብን
የሰፋነው ፡ ሲቀደድ
በሁሉ ፡ ስንናደድ
ችግር ፡ ሲበልጥ ፡ ከአቅማችን
አንተ ፡ ንገሥ ፡ ጌታችን

አዝምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ተመስገን
ምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ይበል

ደስታ ፡ ከእኛ ፡ ሲጠፋ
ሣቁ ፡ ሆኖብን ፡ ዋይታ
መከራችን ፡ ሲበዛ
ግርፊያችንም ፡ ቢበዛ
በረግረግ ፡ ውስጥ ፡ በማዕበል
ጮኸን ፡ ተመስገን ፡ እንበል

አዝምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ተመስገን
ምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ይበል

በደንብ ፡ አርገን ፡ ሠርተነው
ሌላው ፡ መጥቶ ፡ ሲያፈርሰው
በጉያችን ፡ የያዝነው
ሲቀማን ፡ ደግሞ ፡ ሌላው
አንድም ፡ ሳይቀር ፡ በእጃችን
ይክበርልን ፡ ጌታችን

አዝምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ተመስገን
ምን ፡ እንላለን (፫x)
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ይበል