ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው (Men Aynet Feqer New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው? (፪x)
በቀራንዮ ፡ ኮረብታ ፡ ለእኔ ፡ የገለጽከው? (፪x)

የሞተልኝ ፡ ጌታዬን ፡ ኢየሱሴን ፡ ሳስበው
በጣም ፡ ያስደንቀኛል
ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው?

አዝምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው? (፪x)
በቀራንዮ ፡ ኮረብታ ፡ ለእኔ ፡ የገለጽከው? (፪x)

ስለሞተልኝ ፡ ኢየሱስ
ለመናገር ፡ ፍቅሩን
ይቸግራል ፡ ለምላስ
አልችለውም ፡ ፍፁም

አዝምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው? (፪x)
በቀራንዮ ፡ ኮረብታ ፡ ለእኔ ፡ የገለጽከው? (፪x)

በመስቀል ፡ ተቸንክረው
እጆችና ፡ እግሮችህ
ተቀጣህ ፡ ስለእኔ ፡ ኃጢአት
መርገምን ፡ ተሸክመህ

አዝምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው? (፪x)
በቀራንዮ ፡ ኮረብታ ፡ ለእኔ ፡ የገለጽከው? (፪x)

ኃጢአት ፡ ሳይኖርብህ
ቅዱስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ስለእኔ ፡ ኃጢአት ፡ ነው
የሞትከው ፡ በጐልጐታ

አዝምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው? (፪x)
በቀራንዮ ፡ ኮረብታ ፡ ለእኔ ፡ የገለጽከው? (፪x)

ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
የዓለም ፡ ሁሉ ፡ አዳኝ
አስደናቂ ፡ ፍቅርህን
እንዳስበው ፡ እርዳኝ

አዝምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው? (፪x)
በቀራንዮ ፡ ኮረብታ ፡ ለእኔ ፡ የገለጽከው? (፪x)