መልካም ፡ ጋብቻ ፡ ይሁንላችሁ (Melkam Gabecha Yehunelachehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

መልካም ፡ ጋብቻ ፡ ይሁንላችሁ ፡ ጌታ ፡ ይባርካችሁ
ባላችሁ ፡ ነገር ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ ፡ ሰላሙን ፡ ይስጣችሁ
መሪያችሁን ፡ ጌታን ፡ አድርጐ ፡ በማይለወጥ ፡ መዋደድ ፡ ጽኑ
የሠማይ ፡ አፍቃሪ ፡ አባታችሁ ፡ ፍቅሩን ፡ ያብዛላችሁ (፪x)

እረኛችሁን ፡ መምሰል ፡ አትርሱ ፡ ትህትናን ፡ ልበሱ
እርሱ ፡ እራሱን ፡ እንደ ፡ ባሪያ ፡ አድርጐ ፡ እንዳገለገለ
እርስ ፡ በእርሳችሁ ፡ ተከባበሩ ፡ በመደጋገፍ ፡ በቅንነት ፡ ኑሩ
ጠላትም ፡ እንዳያጠቃችሁ ፡ ትዕግሥት ፡ ይሙላባችሁ (፪x)

የአብርሐም ፡ የሣራን ፡ ቤት ፡ ያድርግላችሁ ፡ ፍሬን ፡ ያብዛላችሁ
ዘራችሁ ፡ እንደ ፡ ምድር ፡ ሠራዊት ፡ ይብዛ ፡ እንደከዋክብት
የምድሩን ፡ ፍሬ ፡ ይባርክላችሁ ፡ ጌታ ፡ በፀጋው ፡ ያበልጽጋችሁ
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ አምላካችሁ ፡ ብር ፡ ወርቅ ፡ ይሁንላችሁ (፪x)