From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው
ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ
እግዚአብሔር ፡ ሩህሩህና ፡ መሐሪ ፡ ነው
ከቁጣ ፡ የራቀ ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ ለሚታገሱት ፡ ሁሉ ፡ ቸር ፡ ነው
ምህረቱም ፡ በስራው ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ነው
አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው
ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ
ስለነገሠ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ስላለ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ግርማው ፡ ስለሚያስፈራ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
ስሙ ፡ ታላቅ ፡ ስለሆነ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል
አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው
ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካሉ
አፍም ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ በክብሩ ፡ ያዜማሉ
መላእክት ፡ በሰማይ ፡ በክብሩ ፡ ያዜማሉ
ቅዱሳን ፡ በናፍቆት ፡ በምድር ፡ ይቀኛሉ
አዝ፦ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በኃይሉ ፡ ለገዛው
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ላለው
ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ ፡ አዜማለሁ
|