መድኃኒቱን ፡ ብቻ ፡ ተስፋ ፡ ሲያደርገው (Medhanitun Becha Tesfa Siyadergew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መድኃኒቱን ፡ ብቻ ፡ ተስፋ ፡ ሲያደርገው
በኢየሱስ ፡ የሚያምን ፡ በዕርግጥ ፡ ብጹዕ ፡ ነው

ድካም ፡ ጉስቁልናም ፡ ቢያስደነግጠው
በወንጌል ፡ የተሰጠ ፡ መጽናናቱ ፡ ይብቃው

አንዳንድ ፡ ጊዜ ፡ ክርስቶስ ፡ በግልጥ ፡ ይታየናል
ሌላ ፡ ግን ፡ ፍፁም ፡ ይሰወርብናል

ግን ፡ በሕሊናችን ፡ እንዲህ ፡ ሲለወጥም
ከኢየሱስ ፡ የተሰጠን ፡ ሰላም ፡ አይናወጥም

በኢየሱስ ፡ መሞት ፡ አምላክ ፡ እንደታረቀን
መጽናናት ፡ ሊሆንልን ፡ ወንጌሉ ፡ ነገረን

በደሙ ፡ መድኃኒትም ፡ ተገኝቶልናል
ይህንም ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ መግለጥ ፡ ያስመኘናል

ዘወትር ፡ የአምላኩ ፡ ወዳጅ ፡ ከመሆን
የበለጠ ፡ ብፅዕና ፡ ወዴት ፡ ይገኝ ፡ ይሆን?

እስክንተያይህ ፡ በጭንቀት ፡ ስንኖር
ኦ! ኢየሱስ ፡ ይህ ፡ ሰላምህ ፡ ልባችንን ፡ ይጡር