ማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (Manew Manew Endante Manew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

ባሕርን ፡ ከፍሎ ፡ የሚያሻግረው
ሰማይን ፡ ከፍቶ ፡ መና ፡ የሚያወርደው
በጸናች ፡ ክንዱ ፡ የሚታደገው
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ታላቅ ፡ የሆነው
ከዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ውረድ ፡ የሚለው
እርሱን ፡ ተክቶ ፡ የሚቆም ፡ ማነው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

ክንዱ ፡ አይዝልም ፡ የምናመልከው
ሁሌ ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ የማይታክተው
እኛ ፡ አምላካችን ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው
ተወዳዳሪ ፡ መሳይ ፡ የሌለው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

ውሆችን ፡ በእጁ ፡ የሰፈረውን
ሰማይን ፡ በስንዝሩ ፡ የለካውን
በምን ፡ ምሣሌ ፡ እንመስለው
ይህን ፡ እግዚአብሔር ፡ ማን ፡ እንበለው?

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

በነጻ ፡ ብሉ ፡ ጠጡ ፡ የሚለው
ዋጋ ፡ የማይጠይቅ ፡ ማያስከፍለው
አንድያ ፡ ልጁን ፡ ቆርጦ ፡ የሚሰጠው
ከእግዚአብሔር ፡ በቀር ፡ ወዳጅስ ፡ ማነው?

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው

ሁሌ ፡ ይቅርባይ ፡ ለሚቀርበው
እንደ ፡ ሰው ፡ አይደል ፡ አይሰለቸው
ወረትን ፡ አያውቅ ፡ ጊዜ ፡ አይለውጠው
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝማነው ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)
ከአምላክ ፡ በቀር ፡ አምላክስ ፡ ማነው