ማን ፡ ይገባዋል (Man Yigebawal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ወደ ፡ ተራሮች ፡ ዐይኔን ፡ አንስቼ
ከሚታይ ፡ ነገር ፡ ረዳት ፡ ሽቼ
ቀናት ፡ ቆጠርኩኝ ፡ ግን ፡ የለም ፡ ተስፋ
የሚያጽናና ፡ የሚሰጥ ፡ ፀጋ

አዝ ፣
ማን ፡ ይገባዋል ፡ ለማን ፡ ልናገር?
የልቤን ፡ ሃሣብ ፡ የውስጤን ፡ ነገር
ሃሣብ ፡ ስሜትን ፡ የሚመረምር
ማን ፡ አለ ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ በስተቀር?

ችግሬን ፡ ነገርኩ ፡ ለወዳጆቼ
የውስጤን ፡ ነገር ፡ ሁሉን ፡ አውጥቼ
እንዳልቻሉ ፡ አይተው ፡ ሊያቃልሉልኝ
የርኅራኄ ፡ አምላክ ፡ ጌታ ፡ ይርዳህ ፡ አሉኝ

አዝ ፣
ማን ፡ ይገባዋል ፡ ለማን ፡ ልናገር?
የልቤን ፡ ሃሣብ ፡ የውስጤን ፡ ነገር
ሃሣብ ፡ ስሜትን ፡ የሚመረምር
ማን ፡ አለ ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ በስተቀር?

ከአንተ ፡ እንደሆነ ፡ የሕይወቴ ፡ ቁልፍ
እንደወደድከው ፡ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ እንዳልፍ
አሁን ፡ ተረዳሁ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጌጋ
ድካሜን ፡ አግዝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልምጣ

አዝ ፣
ማን ፡ ይገባዋል ፡ ለማን ፡ ልናገር?
የልቤን ፡ ሃሣብ ፡ የውስጤን ፡ ነገር
ሃሣብ ፡ ስሜትን ፡ የሚመረምር
ማን ፡ አለ ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ በስተቀር?

ነግሬህ ፡ ጌታ ፡ ብዙብዙውን
የሕይወቴን ፡ ጉዳይ ፡ ይህን ፡ ያኛውን
ከመስቀልህ ፡ ሥር ፡ አቅርቤ ፡ ራሴን
እጠብቃለሁ ፡ ልቀበል ፡ ፈውሴን

አዝ ፣
ማን ፡ ይገባዋል ፡ ለማን ፡ ልናገር?
የልቤን ፡ ሃሣብ ፡ የውስጤን ፡ ነገር
ሃሣብ ፡ ስሜትን ፡ የሚመረምር
ማን ፡ አለ ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ በስተቀር?