From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ ፣
ማለዳ ፡ ስነሣ ፡ ጭንቀቴን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልል ፡ ምሥጢረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከኅዘኔ ፡ ገላግለኝ
ምነው ፡ መጨነቄ ፡ ረዳት ፡ እንደሌለው
አሕዛብ ፡ ያውቃሉ ፡ በአንተ ፡ ቅርብ ፡ እንዳለሁ
አጥፍቼም ፡ እንደሆን ፡ ቅጣኝ ፡ እንደልጅህ
የለፋህብኝ ፡ ነኝ ፡ ፈሶልኛል ፡ ደምህ ፡ (፪X)
አዝ ፣
ማለዳ ፡ ስነሣ ፡ ጭንቀቴን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልል ፡ ምሥጢረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከኅዘኔ ፡ ገላግለኝ
በዓይን ፡ የማይታዩ ፡ ሠራዊቶች ፡ አሉኝ
ጠላትን ፡ ከእግሬ ፡ ሥር ፡ የሚያንጋልሉልኝ
ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ለዓለም ፡ ዙሪያ ፡ ሁሉ
አሁን ፡ ብንቀጠቀጥ ፡ ታዲያ ፡ ምን ፡ ይላሉ? (፪X)
አዝ ፣
ማለዳ ፡ ስነሣ ፡ ጭንቀቴን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልል ፡ ምሥጢረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከኅዘኔ ፡ ገላግለኝ
ጉድለቱን ፡ አውቃለሁ ፡ እኔው ፡ ነኝ ፡ ምክንያቱ
ለሥጋም ፡ ለነፍሴም ፡ እሾህ ፡ የሆንኩቱ
አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ምሕረት ፡ የሞላህ
ጠግነኝ ፡ በቁጣህ ፡ አስተምረኝ ፡ እንዳሻህ (፪X)
አዝ ፣
ማለዳ ፡ ስነሣ ፡ ጭንቀቴን ፡ ላዋይህ
ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ
ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልል ፡ ምሥጢረኛም ፡ የለኝ
ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከኅዘኔ ፡ ገላግለኝ
|