ማዳኑን ፡ አይተነዋል (Madanun Aytenewal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ማዳኑን ፡ አይተነዋል
ፍቅሩን ፡ ቀምሰነዋል
ስለዚህ ፡ ክብሩ ፡ ይኸው
ለጌታ ፡ የምንሰጠው

ለውጦናልና ፡ ጌታችን ፡ በስሙ
እመሰክራለን ፡ ሰዎች ፡ ይህን ፡ ስሙ
የቀደመው ፡ ለቅሶ ፡ የቀደመው ፡ ሐዘን
ዛሬ ፡ በኢየሱስ ፡ ደም ፡ ይኸው ፡ ታጠበልን

አዝ፦ ማዳኑን ፡ አይተነዋል
ፍቅሩን ፡ ቀምሰነዋል
ስለዚህ ፡ ክብሩ ፡ ይኸው
ለጌታ ፡ የምንሰጠው

አዳዲስ ፡ ፍጥረታት ፡ ሆነናል ፡ በጌታ
መሠረታችንም ፡ ጠብቋል ፡ አይፈታ
ይህን ፡ ዕድል ፡ ዛሬ ፡ ላላገኙ ፡ ሁሉ
እንመሰክራለን ፡ በስሙ ፡ እንዲድኑ

አዝ፦ ማዳኑን ፡ አይተነዋል
ፍቅሩን ፡ ቀምሰነዋል
ስለዚህ ፡ ክብሩ ፡ ይኸው
ለጌታ ፡ የምንሰጠው

የማይረካ ፡ ስሜት ፡ የማይጠገብ ፡ ረሃብ
የማይሞላ ፡ ምኞት ፡ የማይደርስ ፡ ከግብ
የነበረን ፡ ሁሉ ፡ ዳግመኛ ፡ ተወለድን
ስላየነው ፡ መርካት ፡ እንመሠክራለን

አዝ፦ ማዳኑን ፡ አይተነዋል
ፍቅሩን ፡ ቀምሰነዋል
ስለዚህ ፡ ክብሩ ፡ ይኸው
ለጌታ ፡ የምንሰጠው

ለዓለም ፡ ላንገዣ ፡ ለዓለም ፡ ላንሯሯጥ
አወጣን ፡ ኢየሱስ ፡ ከጨለማ ፡ ከጥልቅ
መዳን ፡ ለተመኘ ፡ አንደኛ ፡ እፎይ ፡ ማለት
ይኸው ፡ የምሥራች ፡ ይቅረብ ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ ፊት

አዝ፦ ማዳኑን ፡ አይተነዋል
ፍቅሩን ፡ ቀምሰነዋል
ስለዚህ ፡ ክብሩ ፡ ይኸው
ለጌታ ፡ የምንሰጠው