ልመናዬን ፡ ስለሰማኝ (Lmenayien Silesemagn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ልመናዬን ፡ ስለ ፡ ሰማኝ
አምላክን ፡ ልወድስ ፡ ነኝ
ረጆች ፡ ሁሉ ፡ ሲርቁብኝ
አምላክ ፡ ኃይል ፡ ረድኤት ፡ ሆነኝ
ክፉን ፡ ሁሉ ፡ ሊያሸንፍ
ሕዝቡን ፡ በሠልፉ ፡ ሊደግፍ

በጤና ፡ ወይ ፡ በሞት ፡ ጊዜ
አለኝ ፡ ተስፋ ፡ በአምላኬ
እርሱ ፡ ረድቶኛል ፡ በጭንቄ
አሁን ፡ ደስ ፡ ይለዋል ፡ ልቤ
ስለዚህ ፡ እርሱን ፡ ላመስግን
እርሱን ፡ ለማገልገል ፡ ልፍጠን

ልዑል ፡ አምላክ ፡ ሁን ፡ ኃይላችን
ሕዝብህን ፡ ከሞት ፡ አድን
ማኅበርህን ፡ በዓለም ፡ አግንን
ጠብቅ ፡ ግዛ ፡ ርስትህን
ተከባከበን ፡ በምድር
አልቀን ፡ በሰማይ ፡ ክብር